አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃጸም አጣሪ ቦርድና ተግባሩ   | ኢትዮጵያ | DW | 31.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃጸም አጣሪ ቦርድና ተግባሩ  

የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላ የሚኖሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ተያያዝ ጉዳዮችን መርምሮ ለምክር ቤቱ ሪፖርት እንድያቀርብ «አጣሪ ኮሚቴ» የማቋቋሙ ተዘግቧል። ይህ የአጣሪ ቦርድ ሰባት ሰዉን የያዘ ስሆን፣ አራቱ ከተወካዎች ምክር ቤት፣ ሦስቱ ሰ ደግሞ የህግ «ባለሙያዎች» መሆናቸዉ ነዉ የተነገረዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:35
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:35 ደቂቃ

አጣሪ ቦርድ መቋቋሙ

በመርህ ደረጃ የትኛዉም አጣሪ ኮምቴ ነፃና ገለልተኛ መሆኑ ቢጠበቅም ሰባቱንም የአጣሪ ኮሚቴ አባላት ከጋዚዉ ፓርቲ ጋር ቁርኝነት እንዳላቸዉ ታዉቋል። ይሁን እንጂ የቦርዱ አባሎች የገዥዊ ፓርቲ አባል መሆናቸዉ የማጣራት ሥራቸዉን እንደማያስተጓግል ይፋ አድርገዋል። የአጣሪ ቦርዱ አባላትንና የመንግስት ኮሙኒኬሼን በኩል የበለጠ መረጃ ለማግኘት ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም። 

ይሁን እንጅ ይህን የአጣሪ ኮምቴ አወቃቀር እንዴት ይመለከቱታል ብለን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉትን ጋዜጠኛ መስፈን ነጋሽን አነጋግረናል። መቀመጫዉን ኖርዌ ባደረገዉ የዜጎች መብት ተሟጋች ዉስጥ በተመራማሪነት የሚያገለግሉት ጋዜጠኛ ነጋሽ አጣሪ ኮሚቴ በየትኛዉም ዓለም ግብ አርጎ የሚያነሱት በተለመደዉ የማጣራት መንገድ ሊጣሩ የማይችሉ ወይም ቢችሉም ጊዜ የሚፈጁ ወይም የጥናት ጥራትን አጠያያቂ የሚያደርጉ ጉዳዮች ስኖሩ እንደምቋቋም ተናግረዋል።

ግለሰቦች ለፓርትያቸዉ ትእዛዝ ተገዢ ናቸዉ ሲሉ የሚገልጹት ጋዜጠኛ መስፍን በአገሪቱ ታሪክም አጣሪ ኮሚቴ ተብዬዎች ከመንግስት ጋር የጠበቀ ቁርኝነት እንዳላቸዉ ተናግረዋል። መንግስት አሁን አገርቱ ዉስጥ ያለዉን ሁኔታ «የማለዘብ»ና ወደ ንግግር መድረክ ለመምጣት የአጣሪ ቦርድ ሲመረጥ «በጣም የተለየ ጥንቃቄና ትኩረት ልሰጥ ይገባ ነበር» ሲሉ አቶ መስፍን ተናግረዋል። 


በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በፌስቡክ ደህረ ገፃችን ያደርግነዉ ዉይይት አስተያየት ከሰጡን ዉስጥ በአገሪቱ ታሪክ አጣሪ ኮሚቴ እየተባለ በተለያዩ ግዜያት ሲነገር እንሰማለን ፤ ተጣርቶ መጨረሻ የሚቀርበው ሪፖርት ስርዓቱን የማያስደስት ነዉ ይላሉ። 

መርጋ ዮናስ

አዘብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች