አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቱሪዝም ላይ ተጽዕኖ አላደረሰም ተባለ | ኢትዮጵያ | DW | 12.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቱሪዝም ላይ ተጽዕኖ አላደረሰም ተባለ

የኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል የሚል ሥጋት በተደጋጋሚ ቢደመጥም ወደ አገሪቱ የሚጓዙ አገር ጎብኚዎች ቁጥር አለመቀነሱን የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ገለጹ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:22

የጎብኚዎች ቁጥር አልቀነሰም - የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት

የኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል የሚል ሥጋት በተደጋጋሚ ቢደመጥም ወደ አገሪቱ የሚጓዙ አገር ጎብኚዎች ቁጥር አለመቀነሱን የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ገለጹ። ይኸን ያሉት በየዓመቱ በጀርመኗ በርሊን ከተማ በሚካሔደው የቱሪዝም ኤክስፖ የታደሙት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ምክትል ሥራ አስኪያጅ  አቶ ይቻል ምሕረት ናቸው።

እንደ አቶ ይቻል አባባል ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ አገር ጎብኚዎች ቁጥር ካለፈው አመት ጋር ሲነፃጸር በ10 በመቶ እድገት አሳይቷል። አሜሪካ እና ብሪታኒያን ጨምሮ በርካታ አገራት ዜጎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ ሲመክሩ ከርመዋል። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የደነገገችው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ምን ተፅዕኖ አሳድሯል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic