አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተራቡ ኢትዮጽያዉያን | ኢትዮጵያ | DW | 04.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተራቡ ኢትዮጽያዉያን

የኢትዮጽያ ግብርና እና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ስለጉዳዩ በሚቀጥለዉ ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጥ ሲገልጽ የአለም የምግብ ድርጅት በበኩሉ ጉዳዩን አሳሳቢ በማለት እርዳታዉን በማሰባሰብ ላይ መሆኑን---

default

ሰሞኑን አንድ የብሪታንያ ጋዜጣ ባወጣዉ እትሙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጽያዉያን የምግብ እርዳታ እንደሚያሰፈልጋቸዉ ገልጾአል። እንደ ጋዜጣዉ መግለጫ የዉጭ እርዳታ ሰጭዎች ባለፈዉ የአዉሮጻዉያኑ አመት ለ12 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ እርዳታ እንዳደረሰ እና እስካሁን የዚህን ግማሽ ያህሉ ህዝብ በአለም የምግብ ድርጅት እርዳታ እንዳለም ይፋ አድርጎአል። በመቀጠል በወቅቱ በአገሪቷ ዉስጥ የተሰበሰበዉ ምርት እጅግ አነስተኛ በመሆኑ አሁንም በርካታ ኢትዮጽያዉያን ረሃብ ላይ እንዳሉ ጋዜጣዉ ይፋ አድርጎአል። የኢትዮጽያ ግብርና እና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ስለጉዳዩ በሚቀጥለዉ ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጥ ሲገልጽ የአለም የምግብ ድርጅት በበኩሉ ጉዳዩን አሳሳቢ በማለት እርዳታዉን በማሰባሰብ ላይ መሆኑን ዛሪ ለዶቸ ቬለ ገልጾአል። ጉዳዩን ጌታቸዉ ተድላ ተከታትሎታል።

Audios and videos on the topic