አስተያየቶች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማሻሻያ ላይ | ኢትዮጵያ | DW | 17.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

አስተያየቶች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማሻሻያ ላይ

የኢትዮጵያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ ስድስት ወራት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ይቀራሉ። መንግስት በዚህ ሳምንት በአዋጅ ላይ ማሻሻያዎችን ማድረጉን አስታውቋል።  የልማት በሚላቸው ቦታዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመከላከል ተብሎ የተጣለዉ ሰዓት እላፊ መነሳቱ ተገልጿል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:53

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማሻሻያ

ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት ለኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም ዘገባ በመስከረም ስለተደነገገው አዋጅ ትግበራ ሲናገሩ «ሰላምና መረጋጋት ተጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም፥ አሁንም ለጸጥታ ስጋት የሚሆኑ ክስተቶች ሙሉ ለሙሉ አለመወገዳቸውን» ጠቅሰዋል። አዋጁ ሊያበቃ ጥቅት ሳምንታት ቢቀሩም ከ80 በመቶ በላይ የሚሆን የማህበረሰቡ ክፍል እንዲቀጥል መፈለጉን ጠቅላይ ሚንስትሩ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ምንስትር ሃይሌማርያም ደሳለኝ አዋጁን በተመለከተ ስለተናገሩት የአንድ አንድ የህብረተሰብ ክፍሎችን አስተያየት ጠይቀን  ነበር። ከመካከላቸው አንዱ ህዝቡ «ምን እንደምፈልገ ግልፅ ነዉ፣ ይታወቃል» የሚሉት እኚህ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉት የአዳማ ነዋሪ ፣  መንግስት ይህን የሚለው «ለራሱ ጥቅም» አዋጁን ለማስቀጠል ፈልጎ ነዉ ይላሉ።

እሮብ እለትም የኢትዮጵያ መንግስት የልማት በሚላቸው ቦታዎች የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመከላከል ተብሎ በአዋጅ ተደንግጎ የነበረዉን ሰዓት እላፊ መነሳቱ ተገልጿል። እንዲሁም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል፣ ብርበራ ማድረግ እና ንብረት መያዝ በተሻሻለው መመሪያ እንዲቀር ተደርጓል ተብሏል። የእነዚህ እገዳዎች መነሳት በህብረተሰቡ  ህይወት ላይ ምን ለውጥ ያመጣል? ሌላው ለአስተያየት ሰጭዎች ያነሳነው ጥያቄ ነበር።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ «መነሳቱ አለመነሳቱ የምፈይደዉ ነገር የለም»፣ ከአዋጁ በፊትም ተመሳሳይ ሁኔታዎች ነበሩ ሲሉ አንድ የዶቼ ቬሌ አድማጭ አስተያየታቸውን በድምጽ ልከውልናል።

በማሻሽያዉም ተነሱ ከተባሉት ክልከላዎች ውስጥ በራድዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በጽሁፍ፣ በፎቶግራፍ፣ ቲያትር እና ፊልም የሚተላለፉ መልዕክቶች ላይ የተጣለው እገዳ ይገኝበታል። ለመሆኑ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ፀሀፊዎችና ተጠቃሚዎች ማሻሺያውን እንዴት ይመለከቱታል?

ብዙዎች እንደሚሉት ይህ ክልከላ  ሃሳብን በነፃ የማንሸራሸር መብትን በሰፊው አግዶ ነበር። ይሁን እና  እኚህ የአዲስ አበባ ነዋሪ እና የማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ተጠቃሚ  የእገዳው መነሳት ጥቅም አልታየኝም ይላሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንም በተለያዩ አከባቢዎች ችግር እንዳለ  ለችግሩም መፍትሄ ለማምጣት ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል። ጥናቱ ተጠናቆ ለተወካዮች ምክር ቤት ከቀረበ በኋላ የአዋጁ መራዘም አለመራዘም እንደሚወሰንም ተናግረዋል።

መርጋ ዮናስ

ሕሩት መለሰ 

Audios and videos on the topic