አስተያየት በጄኔራሎች መልዕክት ላይ | ኢትዮጵያ | DW | 05.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

አስተያየት በጄኔራሎች መልዕክት ላይ

ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ /ሕወሐት/ ለሁለት ሲከፈል ከሥልጣን የተባበረሩት ሁለት የቀድሞ የኢሕአዲግ ታጋዮችና የጦር ጄኔራሎች በቅርቡ ስለ ሐገሪቱ ፖለቲካ ከረር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:50

የጄኔራሎች መልዕክት

የቀድሞዉ የአየር ሐይል አዛዥ ሜጀር ጀነራል አበበ ተ/ሃይማኖት <<ኢህአዴግ ህገ መንግስቱን እየሸረሸረ ነው>>፤ <<ህገ መንግስቱን የሚጻረረው የሠራዊት ግንባታ ሰነድ ይታገድ>> እና <<ደርግነት እያቆጠቆጠ ነዉ፤ ህዝቦች ጠንቀቅ በሉ!>> የሚሉ አስተያየቶችን ሰንዝረዋል። የቀድሞዉ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሌትናንት ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ ደግሞ «አገርቱ ዉስጥ አሁን ያለዉ የፖሊቲካ ሁኔታ ወደ ብጥብጥ ሊያመራ ስለሚችል መንግስት በሰላማዊ መንገድ አገሪቱን ወደ ዲሞክራስያዊ ስርዓት መዉሰድ አለበት» ይላሉ።


እንደዚህ አይነት አስተያየቶች አሁን ለምን ብቅ አሉ» ብለዉ የሚጠይቁ አሉ። የጄኔራሎቹን መልዕክትና በመልዕክቶቹ ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን እንዴት ይመለከቱታል ብለን እኛም ከአድማጮቻን አስተያየት ሰብስበናል።


በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሠረት አረጋ ጄኔራሎቹ ያስተላለፉት መልዕክትም ሆነ አቋም የግለሰብ አስተያየት ነዉ እንጅ ሁሉንም ይወክላል ይላሉ። ይሁን እንጅ አሁን አገሪቱ ዉስጥ ያለዉ ተቃዉሞ ከባድ መሆኑን ጠቅሶ በአዲስ አበባም አሰፈሪ ሁኔታ ነዉ ያለዉ ይላሉ።

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ነዋሪ የሆኑት አቶ ኑርዬ ዳዉድ የአቶ መሠረትን ሃሳብ ተጋርተዉ የጄኔራሎቹ መልክት ትክክል ነዉ ሲሉ ለደቼ ቬሌ ተናግረዋል።

በፌስቡክ ደረገፃችን ላይም ይሄን ጉዳይ በተመለከተ አዋያይተን ነበር። አስተያየተቸዉን ከሰጡን ዉስጥ የኢትዮጵያ መንግስት <<ሁሉም በማንነቱ እንዲኮራ እና በእኩልነት፣ በመከባበርና በመፈቃቀር እንዲኖር>> ስላዳረገ ለኢህአዴግ ረጅም እድሜ የተመኙለትም አሉ። ሌሎች ደግሞ ሁሌ ደርግን ለመጥፎ ነገር ምሳሌ ማድረግ ጥቅሙ ምንድነዉ፣ የጄኔራሎቹም መልዕክት <<ሕውሐት ለመውደቅ መንገዳገድ ስለጀመረ ከውድቀቱ ለማዳን አስበው እንጂ ለሕዝቡ ተጨንቀው አይመስለኝም>>፣ <<ሌባ ተማክሮ ይሰርቃል ሲካፈል ይጣላል ነው ነገሩ ። ትክክል ብልዋል ግን። ዛሬ አልነበረም ይህንን የሚነገሩት አሁንማ ጉርሻው ስለቀረባቸው ነው>> ሲሉ አስተያየታቸዉን ሰንዝረዋል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic