አስተያየት በአቶ ኃይለ ማርያም ሥልጣን መልቀቅ ላይ | ዓለም | DW | 16.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

አስተያየት በአቶ ኃይለ ማርያም ሥልጣን መልቀቅ ላይ

« ጉዳዩ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ነው። ሆኖም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን መልቀቅ ለወደፊቱ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ተስፋን የሚያበረታታ ነው» የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:23

የአሜሪካን መንግሥት እና የኢትዮጵያውያን አስተያየት

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሥልጣን እለቃለሁ ማለታቸው በጎ ነው ሲሉ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተናገሩ። ሆኖም ለዶቼቬለ አስተያየታቸውን የሰጡት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን የህዝብ ጥያቄ የግለሰብ ለውጥ ሳይሆን የስርዓት ለውጥ መሆኑን ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ዶቼቬለ አስተያተቱን የጠየቀው የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ጉዳዩ የሀገር ውስጥ ጉዳይ መሆኑን አስታውቆ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልቀቅ ለወደፊቱ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ተስፋን የሚያበረታታ ነው ማለቱን ከዋሽንግተን መክበብ ሸዋ ዘግቧል። 

መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ 
 

Audios and videos on the topic