አስተያየት በመገናኛ ብዙሃን ም/ቤት ምሥረታ | ኢትዮጵያ | DW | 15.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አስተያየት በመገናኛ ብዙሃን ም/ቤት ምሥረታ

ለበርካታ አመታት ሲወድቅ ሲነሳ የከረመው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ሰሞኑን ተመሥርቷል። ምክር ቤቱ በጋዜጠኞች መብትና የሥነምግባር ጉዳይ ላይ ትኩረት በማድረግ ችግሮች ሲፈጠሩ የማረምና የማስተካከል ኃላፊነት እንደሚኖረው ተነግሯል።

ከምሥረታው በፊት በርካታ አጨቃጫቂ ጉዳዮች ይቀርቡበት የነበረው የመገናኛ በዙሃን ምክር ቤት ከምሥረታው በኋላም ቢሆን ሁሉንም ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሀን ድርጅቶችን ይሁንታ ያገኘ አይመስልም። ገለልተኛ የሆኑም ሆነ አፍቃሬ መንግሥት የሆኑ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን ከምክር ቤቱ አባልነት ራሳቸውን አግልለዋል።

ቀደም ባሉ ጊዜያት ምክር ቤቱን ለመመሥረት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጋዜጠኞችም በጥርጣሬ ይመለከቱታል። ለጋዜጠኞች የሚሟገቱ እንደ ሲፒጄ ያሉ ድርጅቶችም ምሥረታዉን በርቀት እየተከታተሉት እንደሆነ ተነግሯል። ከዋሽንግተንዲሲ ወኪላችን ዝርዝሩን ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic