አስም ምንድነዉ? | ጤና እና አካባቢ | DW | 13.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

አስም ምንድነዉ?

የመተንፈሻ አካላትን ከሚጎዱ ሕመሞች አንዱ አስም ነዉ። የበርካቶች የጤና ችግር እንደሆነ የሚነገርለት አስም መንስኤዉ በትክክል ይህ ነዉ ተብሎ እንደማይታወቅ የሕክምና ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

ስለበሽታዉ ማብራሪያ የሰጡን የሳንባ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ጌታቸዉ አደራ እንደሚሉትም አስም ሊከላከሉት እንጂ ሊያድኑት የማይችል በሽታ ነዉ። አስም በዘር የሚተላለፍ በሽታ ይሁን እንጂ ከሰዉ ወደሰዉ አብሮ በመኖር በትንፋሽ ግን አይጋባም።

ዶክተር ጌታቸዉ አክለዉ እንደገለፁት አስም ሊዲን የማይችል ሆኖም ሊቆጣጠሩት የሚቻል በሽታ መሆኑን በሚገባ አዉቆ ሕመሙን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ መነሻ ምክንያቶችን መራቅ ብቸኛ እና ዋነኛ መከላከያ መንገዱ ነዉ። የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ለአንዳንዶች የሚረዳ መሆኑ ቢታመንም እንደአስሙ ዓይነት የማይስማማቸዉ እንደዉም ሊያባብስባቸዉ የሚችሉ መኖራቸዉንም መገንዘብ እንደሚያስፈልግም ሃኪሙ አስረድተዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic