አሳዛኙ የኤርትራውያን ስደተኞች ዕጣ ያስከተለው ወቀሳ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 24.08.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

አሳዛኙ የኤርትራውያን ስደተኞች ዕጣ ያስከተለው ወቀሳ

በሜዴትራንያን ባህር በኩል በጀልባ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሞከሩ 73 ኤርትራውያን ስደተኞች የሚደርስላቸው አጥተው በውሀ ተበልተው መቅረታቸው አውሮፓውያንን ለክፉ ትችት ዳርጓል ። ከተችዎቹ አንዷ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ናት ።

default

በጀልባ ይጓዙ የነበሩት ስደተኞች የሚታደጋቸው አጥተው በረሀብና በውሀ ጥም መሞታቸው ያስቆጫት ቤተክርስቲያኗ ሠለጠነ የሚባለው ህብረተሰብ ከዕውቀት ዕጦት ብቻ ሳይሆን በራስ ወዳድነት የውጭ ዜጎችን ያለመቀበል አዝማሚያ በማሳየት ወቅሳለች ። የትች ናዳ የወረደባት ኢጣልያ እንዲሁም ማልታ በስደተኞቹ ጉዳይ እየተነታረኩ ነው ። ኢጣልያ ችግሩን የመወጣቱ ሀላፊነት የአውሮፓ ህብረት ድንበር ለሆኑት እንደ ኢጣልያ ለመሳሰሉት አገራት ብቻ መተው የለበትም ስትል ትከራከራለች ። የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ በሀያ ሰባቱ አባል ሀገራት የሚሰራ አንድ ወጥ የስደተኞች ህግ በማርቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቋል ።

ጌታቸው ተድላ ሂሩት መለሰ