አሳሳቢው የኤቦላ ወረርሽኝ እና ማከላከያው ጥንቃቄ | ጤና እና አካባቢ | DW | 08.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

አሳሳቢው የኤቦላ ወረርሽኝ እና ማከላከያው ጥንቃቄ

በምዕራብ አፍሪቃ ካለፈው መጋቢት ወር ወዲህ በተከሰተው እና በዓለም እስከዛሬ አስከፊ መሆኑ በተነገረለት የኤቦላ ወረርሽኝ የ3,431 ሰዎችን ሕይወት ማጥፋቱን፣እንዲሁም፣ በጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴየራ ልዮን ወደ 7,470 ሰዎች ደግሞ በኤቦላ አስተላላፊ ተሀዋሲ መያዛቸውን

የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት አስታውቋል። ኤቦላ በሰዎች ላያ እያደረሰው ካለው ጥፋት ጎን፣ እአአ እስከ 2015 ዓም መጨረሻ ድረስ በምዕራብ አፍሪቃ ኤኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ኪሳራ 32,6 ቢልዮን ዩኤስ ዶላር ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ይኸው ገዳይ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ ሃገራት ሕዝባቸው አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማንቃት እንደሚኖርባቸው ዶይቸ ቬለ ያነጋገራቸው አንድ የጤና ባለሙያ አሳስበዋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic