አሳሳቢው የማንዴላ ጤንነት ይዞታ | አፍሪቃ | DW | 27.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

አሳሳቢው የማንዴላ ጤንነት ይዞታ

ከሦስት ሣምንታት ወዲህ በፕሪቶርያ ሐኪም ቤት የሚገኙት የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ኔልሰን ማንዴላ ጤንነት ዛሬም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ከደቡብ አፍሪቃ ዛሬ ከትናንቱ የተለየ ጥሩም መጥፎም ዜና የለም።አንጋፋዉ የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ እና የመጀመሪያዉ የሐገሪቱ ጥቁር ፕሬዝዳት ኔልሰን ማንዴላ ዛሬም እንደትናንቱ በጠና እንደታመሙ ነዉ።ዛሬ ጠዋት ማንዴላን የጎበኙት የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳት ጄኮብ ዙማ እና ከማንዴላ ልጆች አንዷ የዘጠና አራት ዓመቱ አዛዉንት ከትናንቱ ሻል ብሏቸዉ እንደነበር አስታዉቀዉ ነበር።ይሁንና ፕሬዝዳት ዙማ ራሳቸዉ የአንጋፋዉን መሪ ሁኔታ በቅርብ ለመከታተል በሞዛምቢክ ሊያደርጉት የነበረዉን ጉብኝት ሠርዘዋል።ደቡብ አፍሪቃዉያን አንጋፋዉ የጥቁሮች መብትና የነፃነት ታጋይ የተኙበትን ሐኪም ቤት ከበዉ ለማንዴላ ያላቸዉን ፍቅርና ክብር እየገለፁ ነዉ።ሕፃናትም-ጭምር

«እኛን ነፃ አዉጥተዉናል።አሁን ሁላችንም እንደምናፈቅራቸዉ መግለፅ እንወዳለን።---ለኔ ጀግናዬ ናቸዉ።ምክንያቱም ለነፃነት ተፋልመዋልና።ለኔ እንደ አባት ናቸዉ።ማንዴላን እወዳቸዋለሁ።በጣም እወዳጀዋለሁ።ለሰዎች የሚቆረቆሩ ሰዉ ናቸዉ።ለሕፃናትም ለሌሎች ሰዎችም ደግ ናቸዉ።ይወዱናል።»

ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከጁሐንስ በርግ የሚወጡ ዘገቦች እንደጠቆሙት ማንዴላ ዛሬ ጠዋት መለስ ያለላቸዉ ቢመስልም ከቀትር በኋላ ግን ጤናቸዉ ትናንት እንደነበረዉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነዉ።በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ደቡብ አፍሪቃዉያን ማንዴላ የተኙበትን ሐኪም ቤት ከበዉ ፀሎት ምሕላቸዉን ዛሬም ለአስራ-ዘጠነኛ ቀን እንደቀጠሉ ነዉ።

ለሳንባ ሕመም ሕክምና እየተደረገላቸው ያሉትን የ 94 ዓመቱ የኖቤል ሰላም ተሸላሚ እና የአፓርታይድ ታጋይ ማንዴላን ጤንነት ይዞታ መላው ዓለም በስጋት እየተከታተለው ነው። ደቡብ አፍሪቃውያን በጠቅላላ የተወዳጁ መሪያቸው ጤንነት እንዳሳሰባቸው ከዚያ የሚደርሱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። የማንዴላን ጤንነት ይዞታ በተመለከተ በሀገሪቱ ስለሚታየው ሁኔታ እንዲነግሩኝ በደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ሊቀመንበር የሆኑትን በፕሪቶርያ የሚገኙትን አቶ ታምሩ አበበን ቀደም ሲል ስልክ በመደወል ጠይቄአቸው ነበር።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች