አሰቃቂዉ የመስከረም አንድ ትዉስታ ለአሜሪካዉያን | ዓለም | DW | 11.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

አሰቃቂዉ የመስከረም አንድ ትዉስታ ለአሜሪካዉያን

በኒዉ ዮርኩ አለም ንግድ ማዕከል ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ሁለት የሰዉ ማመላለሻ ቦይን ጀቶች አንጉደዉት ከወደመ ዛሪ ስምንተኛ አመቱን ያዘ። በአሸባሪዎች ተገዶ ተሳፍሪዎችን እንደጫነ መንትያዎቹ ህንጻዎች በመባል የሚታወቀዉን የአለም የንግድ መአከል ህንጻ አመድ ሲያደርገዉ የሶስት ሽህ ህዝቦችም ህይወት አልፍል።

default

የዚህን የአሸባሪዎች ጥቃት ለጥቂት ያመለጠ ደግሞ ዛሪም ይህ አሰቃቂ ትዉስታ የየቀን ህይወቱ ላይ ጋሪጣ ጥሎበታል። ዛሪ ይህንን አሰቃቂ አደጋ በማሰብ እና ሙታንን ለማስታወስ ዩናይትድ ስቴትስ ከጠዋቱ 8:46 ላይ የሃዘን ጸጥታ ስነ-ስርአት አካሂዳለች

በዩኤስ አሜሪካ በተለይም በኒዉዮርክ ከተማ የዛሪ ስምንት አመት አሸባሪዎች ባደረሱት ጥቃት የሶስት ሽህ ህዝቦች ህይወት የቀጠፈበት አስከፊ ክስተት ለአሜሪካዉያኑ አሁንም ከባድ የሚያመረቅዝ ቁስል ነዉ። በተለይ ለኒዉዮርክ ነዋሪዎች ይህ አስከፊ የሆነ ድንገተኛ ገጠመኝ ዛሪም ከስምንት አመት በኻላ አብሮ ይገኛል።

World Trade Center: Menschen auf der Flucht

በጎርጎረሳዉያኑ አቆጣተር አስራ አንደኛ ወር ላይ በመስከረም 2001 አ.ም ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ላይ የደረሰዉ አስከፊ ገጠመኝ

«ይህ አዉሮፕላን ሲበር ሳይ በጣም ያስደነግጠኛል። በፊት ግን የአዉሮፕላንም ሆነ የባቡር ጩኸት አያስደነግኝም ነበር። ብቻ ከፍተኛ ድምጽ ያለዉ የሞተር ጩኸት ከመስከረሙ ክስተት በኻላ በጣም ያስደነግጠናል»


የአርባ አመቱ ሚሻየል ዶቢ የመኖርያ እና የስራዉ ቦታ በኒዉዮርክ ከተማ ነዉ። የዛሪ ስምንት አመት ሚሻየል በደቡብ አቅጣጫ ላይ በነበረዉ በአለም የንግድ ማእከል ህንጻ ስድሳኛዉ ፍቅ ላይ የቅየሳ ስራዉን በማከናወን ሳለ ነበር በሰሜን በኩል ባለዉ በሁለተኛዉ የኒዉዮርኩ ህንጻ ላይ የህዝብ ማመላለሻዉ አዉሮፕላን ሰማይ ጠቀሱን ህንጻ ለሁለት ገንጥሎ ገብቶ መጋየት የጀመረዉ። በደቡብ አቅጣጫ ህንጻ ላይ ስራዉን ይሰራ የነበረዉ ሚሻኤል እና የስራ አለቃዉ ይህንን አስደንጋጭ ሁኔታ እንዳዩ ያሉበትን ህንጻ ለመልቀቅ ወስነዉ ከስድሳኛዉ ፎቅ ተነስተዉ በደረጃዉን ይዘዉ ቁልቁል እየሮጡ በመዉረድ ላይ ሳሉ በአሸባሪዎች ተገዶ እና ተጠልፎ የነበረዉ ሁለተኛዉ አዉሮፕላን እነሱ የነበሩበትን የደቡባዊዉንን የንግድ መአከል ያነጎደዉ።

«ትዝ ከሚለኝ ነገር እንዴት እየተንደረደርኩ ያንን ደረጃ እወርድ እንደነበር፣ ከዝያም ሰዎች ምንድን ነዉ ምንድነዉ እንደዚህ ሃይለኛ የሆነ ድምጽ የተሰማዉ እያሉ ሲጠይቁ እና እርስ በራሳችን ይህንኑ ጥያቄእ እየጠየቅን ስንወርድ ነዉ። ይህ ጩኸት እና ሃይለኛ የሆነ ድምጽ አሁንም ከአእምሮዪ አልጠፋም»

ሚሻየኤልና የስራ ባልደረቦቹ ከስድሳኛዉ ፎቅ በመንደርደር ህንጻዉ ለሁለት ሳይገመስ እምድር ደርሰዉ በመንደድ እና መመገመስ ላይ የነበረዉን ህንጻ በፎቶ ለመቅረጽም ደርሰዉ ነበር። በዝያን ሰአት ግን ሚሻኤል ከምን አይነት ትልቅ አደጋ እንዳመለጠ እንዲሁም ከህንጻዉ ወጥቶ ህንጻዉ አጠገብ ቆሞ ፎቶ ሲቀርጽ ምን አይነት ትልቅ አደጋ ሊያጋጥመዉ እንደሚችል አልተረዳም ነበር። የንግድ ማእከሉ በአሸባሪዎቹ ሲራ በሁለቱ አዉሮፕላኖች ጋይቶ እና ተቃጥሎ ለሁለት ተገምሶ ሲወድቅ ሚሻኤል እዝያዉ አደጋ የደረሰበት አካባቢ ነበር። በዝያን ግዜ ጭስ እና በቧራ ሰበብ የተጎዳዉ የመተንፈሻ አካሉ፣ አሁን በየቀኑ ጠዋት መድሃኒት እንዲወስድ አስገድዶታል። መድሃኒቱን በዋጠ ቁጥርም የሚያስታዉሰዉ የዛሪ ስምንት አመቱን አሰቃቂ የመስከረም ክስተትን ነዉ።

«አሁንም አሰቃቂ የሆነዉ ትዝታ ከጭንቅላቴ አልወጣም ምንም እንኳ እንደ በፊቱ በየቀኑ ባይሆንም»

Obamas 11. September Gedenken 2009

የዛሪ ስምንት አመት አሸባሪዎች ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ላይ የኒዉዮርክን የንግድ ማእከል ሲያጋዩ ሶስት ሽ ህዝብ ያለቀበትን ሁኔታ ለማስታወስ ዛሪ በዩኤስ አሜሪካ 8:46 ላይ የሃዘን መግለጫ ስነ- ስርአት ተደርገዋል። አሸባሪዎች የዛሪ ስምንት አመት በዛሪዋ እለት አራት አዉሮፕላኖችን በመጥለፍ መንትያዎቹ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች በማለት የሚታወቁትን የአለም የንግድ ማእከል ቢሮን፣ በሁለት አዉሮፕላን በማንጎድ፣ ሶስተኛዉን ዋሽንግተን በሚገኘዉ የአገሪቷ መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን ላይ፣ እንዲሁም አራተኛዉ አዉሮፕላን ፔንስልቬንያ ግዛት ላይ በመጣል አደጋ ማድረሳቸዉ ይታወሳል።


በኒዮርክ በአለም የንግድ መአከል የቅየሳ ስራ ተግባሩን ያከናዉን የነበረዉ ሚሻኤል ከዛሪ ስምንት አመቱ የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ የአስም በሽተኛ ቢሆንም ትዳር መስርቶ የልጅ አባት ሆንዋል። እንደ ሚሻኤል ገለጻ ከዚህ አሰቃቂ ጥቃት ወዲህ አገሪቷ ላይ ትልቅ ለዉጥ ይታያል።
ህዝቡ አንድ ላይ የመሆን ሁኔታ የታየበት ይመስላል። ምንም እንኻ በርካታ ህዝቦች እንዲህ አይነቱ የአሸባሪዎች ጥቃት ፈጽሞ ሊደገም አይችልም፣ የጸጥታዉ ሁኔታ የተረጋገጠ ነዉ ብለዉ ቢያምኑም። ሚሻኤል ግን የዛሪ ስምንት አመት ጠዋት ስራዪን ስጀምር የተከሰተዉ አይነት ሁኔታ አሁንም ይከሰታል የሚል ፍርሃት በየቀኑ እንዳለበት በግልጽ ይናገራል።

አዜብ ታደሰ/ ነጋሽ መሃመድ/ ሂሩት መለሰ