አርቲስት ይግረም ደጀኔ | ባህል | DW | 08.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

አርቲስት ይግረም ደጀኔ

በበርካታ አጫጭር እና ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በትወና ተሳትፏል። በተለይ በቅርቡ በቴሌቪዥን በተላለፈው የ«ሰው ለሰው» ተከታታይ ድራማ እና አሁን በመታየት ባለው «ሞጋቾቹ» ድራማ ይታወቃል። መንፈሣዊ ዜማዎቹም በኢንተርኔት እና በሲዲ ተሰራጭተዋል።

default

ከ40 በላይ በሚሆኑ አጫጭር የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በትወና ተሳትፏል። የተለያዩ ገፀ-ባሕርያትን ተላብሶ የተጫወተባቸው ፊልሞች 31 ደርሰዋል። በመድረክ ተውኔት ላይ ደግሞ ለ7 ጊዜያት ተውኗል። በትወና የተሳተፈባቸው አጫጭር እና ተከታታይ የሬዲዮ ድራማዎች በርካታ ናቸው። ወደ ጥበቡ ዓለም ያመጣው መንገድ መነሻው ከቤተክርስቲያን የሠንበት ትምህርት ቤት አካባቢ ነው።

አርቲስት ይግረም ደጀኔ አስቴር ይባላል። «ሞጋቾቹ» በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ከተጫወተው የቀነጨብነውን ነው ያሰማናችሁ። ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ከተማ፥ አሮጌው ቄራ አካባቢ ነው። ይግረም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በጆን ኤፍ ኬኔዲ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በጥቁር አንበሣ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ1992 ዓም አጠናቋል።

የጥበቡን ዓለም ሲቀላቀል በዚያው ለመዝለቅ ወስኖ አልነበረም። ምናልባትም ለአንድ ወር ያህል አይቼ እተወዋለሁ ብሎ ለጀመረው የትወና ሙያ ዛሬ ጠልቆ ገብቶበታል።

ይግረም ከ2000 ዓም ወዲህ ወደ ሙያው ብቅ ያሉ ወጣቶች በተለይ የካሜራ እና የኤዲቲንግ ጥበብ ችሎታቸው ላቅ ያለ መሆኑ እንደሚያስደስተው ገልጧል። ሆኖም በትወናው በኩል ተመሳሳይ ሰዎች አስቂኝ የፍቅር ፊልሞች ላይ መደጋገማቸው እና የተለዩ ታሪኮች በቂ ተመልካች የማጣታቸው ጉዳይ እጅግ ሳያሳስበው አልቀረም። የተዋንያኑ የርስ በርስ ግንኙነትም ያን ያህል አጥጋቢ አለመሆኑ ጥበቡን ሳይጎዳው እንዳላለፈ ጠቁማል። ሌሎች ሣንካዎችንም ይጠቃቅሳል።

ሙሉውን ዘገባ ለማድመጥ ከታች የሚገኘውን የድምፅ ማጫወቻውን ይጫኑ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተክሌ የኋላ