1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን እንዴት ይገልፁታል?

ሐሙስ፣ ሰኔ 25 2012

አርስቲስት ሃጫሉ ዘፈኖቹ ተወዳጅነቱ ኦሮምኛ ቋንቋን በሚያዉቀዉ ማኅበረሰብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን፤ በተለይ ድምፁ ተስረቅራቂ ዜማዉ ወኔ ቀስቃሽ፤ አልያም አፍቃሪ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ። ሙዚቃን በመድረክ ይዞ ሲቀርብም ዜማዉን ግጥሙን በመድረኩ ሲኖረዉ ይታያል።

https://p.dw.com/p/3ei9A
Äthiopien Hachalu Hundessa, ermordeter Künstler
ምስል Leisa Amanuel

ሃጫሉ በመድረክ ሲቀርብ ዜማዉን ግጥሙን ይኖረዋል

«አዎ እኔ የሃጫሉ ጓደና ነኝ ግን እኔ ታላቁ ነኝ። የታላቅ ወንድሙ ጓደኛ ነኝ። ግን አንድ ሰፈር ነዉ ያደግነዉ። በሥራዉ ሁሌም አዋቂ ልጅ፤ አፍቃሪ ልጅ። ጥጃ ሲጠብቅም ፤ ዓይን የሚያርፍበት ከሰፈርም ልጅ ቀልድ የሚያዉቅ ፤ ልብ የሚወስድ ልጅ ነበር። እንደዉ የተቀባ ልጅ ነበር»

ወይዘሮ ብርኃኔ ቤካ ይባላሉ። የኢትዮጵያዊዉ ድምፃዊ፤ የሙዚቃ ደራሲና በኦሮሞ ትግል ትልቅ ተፅኖን ያሳረዉ የተወዳጁ ሃጫሉ ሁንዴሳ አብሮ አደግ ናቸዉ። ወይዘሮ ብርኃኔ እንደሚሉት በአምቦ ቀደም ሲል 06 ቀበሌ በሚል በሚታወቀዉ አካባቢ በአሁኑ አራዳ ኮልፌ ሰፈር በመባል በሚጠራበት አካባቢ ከሙዚቀኛ ሃጫሉ ጋር አብረዉ አድገዋል። በዝያዉ በአምቦ አራዳ ኮልፊ በሚባለዉ አካባቢ በሚገኘዉ ኦዶ ሊበን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም አብረዉ ተምረዋል። ይሁንና ይላሉ ወይዘሮ ብርኃኔ ሃጫሉ በጣም ታናሼ ነዉ፤ እኔ የታላቅ ወንድሙ እኩያ እና የታላቅ ወንድሙ ጓደኛ ነኝ ። አርስቲስት ሃጫሉ ዘፈኖቹ ተወዳጅነቱ ኦሮምኛ ቋንቋን በሚያዉቀዉ ማኅበረሰብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን፤ በተለይ ድምፁ ተስረቅራቂ ዜማዉ ወኔ ቀስቃሽ፤ አልያም አፍቃሪ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ። ሃጫሉ ሁንዴሳ ሙዚቃን በመድረክ ይዞ ሲቀርብም ዜማዉን ግጥሙን በመድረኩ ሲኖረዉ መታየቱ የሁሉን ሰዉ ልብ የሚሰርቅ መሆኑን በተለያዩ መድረኮች አስመስክሮአል። ወይዘሮ ብርኃኔ ቤካም ሃጫሉ አብሮአቸዉ ስላደገ ብቻ ሳይሆን ዘፈኖቹ የሕይወት፤ የትግል ፤ የፍቅር ፤ ሃገራዊ ስሜት ቀስቃሽ በመሆናቸዉ ሙዚቃዉን በመስርያ ቤታቸዉ ፤ በመኪና ዉስጥ ሁሉ ያዳምጡታል።

« ሃጫሉ ሙዚቃዉን ለራሱ ነዉ የሚጽፈዉ። በዉስጡ ያለዉን ፤ ለራሱ ለሕዝቡ ብቻ ሳይሆን፤ ለዓለም ማኅበረሰብ እንዲወደድ፤ ተቀባይነት እንዲያገኝ አድርጎ ነዉ ጽፎ የሚያዜመዉ።እኔ ሁሌ የእሱን ሙዚቃ ነዉ የማዳምጠዉ። » የሃጫሉ የቅርብ ባልንጀራ የሕክምና ባለሞያዉ አቶ ሌሊሳ አማኑኤል ይባላሉ ። አቶ ሌሊሳ አርቲስት ሃጫሉን ለረጅም ዓመታት ያቁታል።  ያለፈዉ ሰኞ ሰኔ 23 /2012 ዓም ምሽት 3 30 ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ የተነገረዉ የ 36 ዓመቱ  አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ዛሬ ሰኔ 25 / 2012 በአምቦ፤ እየሱስ ቤተ-ክርስትያን ሥርዓተ ቀብሩ ተፈፅሞአል። አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ባለትዳርና የሦስት ሕጻናት ልጆች አባት ነበር። ሙሉ ስርጭቱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ