አርምሞ ወይም ሜዲቴሽን | ባህል | DW | 14.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

አርምሞ ወይም ሜዲቴሽን

ዮፍታሔ ማንያዘዋል ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ነው። በአሁኑ ሰዓት በመቀሌ ዩንቨርሲቲ የስድስተኛ አመት የስነ ህንፃ ወይንም አርክቴክቸር ተማሪ ነው። ከያዝነው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ደግሞ ከትምህርቱ ጎን ለጎን በተባባሪ አስተማሪነት ያገለግላል። ዮፍታሔ ከ13 አመቱ ጀምሮ ነው የአርምሞ ወይንም ሜዲቴሽን ስልት መጠቀም የጀመረው።

ይህ ስልት በእስያ እንዲሚገኙ አገሮች እንብዛም ኢትዮጵያ ውስጥ የተለመደ አይደለም። ዮፍታሔ  «እናቴ ናት ከጥሞና ጋ ያስተዋወቀችን» ይላል።  ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የተለያዩ የጥሞና ክህሎቶችን ማወቅና መተግበር ጀምሯል። ይህም ዮፍታሔ እንደሚለው አሁን ለሚማረው ትምህርት ትልቅ አስተዋፅዎ አድርጎለታል። ዮፍታሔ በተለያዩ መንገዶች ስልጠና ይወስዳል፣  እውቀትንም ለሌሎች ያካፍላል። ዮፍታሔ በጥሞና ከራሱ ጋ ሲወያይ አስር አመት ሆኗቷል። ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ ነግሮናል።  ዮፍታሔን ለየት የሚያደርገው ሌላው ነበር በየቀኑ ለሚያከናውናቸው ነገሮች ዕቅድ ማውጣቱ ነው።  ወጣቱ  ያለፈው አመት አንድ « ዊዝደም ስቴፕስ» የሚባል የተማሪዎች እንቅስቃሴ አቋቁሟል። አላማውን ባጭሩ አብራርቶልናል።

ወጣቱ እስካሁን ሰልጥኖ እና አሰልጥኖ ያገኛቸው 50 የምስክር ወረቀቶች አሉት። ከነዚህም ውስጥ የቋንቋ፣ የስፖርት እና የውድድር የምስክር ወረቀቶች ይገኙበታል።

በቅርቡ ከ700 የዮንቨርሲቲ ተማሪዎች  ጋ በፈጠራ ክህሎት የፁሁፍ ውድድር ተወዳድሮ በማሸነፉ ወደ ታይላንድ ለሽልማት ተጉዞ ነበር።  ዮፍታሔ በአሁኑ ሰዓት « ሸጋ ፌስት ፎር ግሬትነስ» የተሰኘ አገር አቀፍ ስልጠና ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው። ይህም ትምህርቱን ሲያጠናቅ ወደፊት ለማድረግ ካሰበው አላማ ጋ የተጣመረ መሆኑን ገልፆልናል።

ስለአርምሞ ወይንም ሜዲቴሽን ስልት ተማሪ  -ዮፍታሔ ማንያዘዋል የሰጠንን ሰፊ ማብራሪያ ከዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic