አራት የአፍጋኒስታን እስረኞች ከጓንታናሞ ነፃ ተለቀቁ | ዓለም | DW | 21.12.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

አራት የአፍጋኒስታን እስረኞች ከጓንታናሞ ነፃ ተለቀቁ

ዬኤስ አሜሪካ ጓንታናሞ ኪዩባ በሚገኘዉ ወታደራዊ እስር ቤቷ የያዘቻቸዉን አራት የአፍጋኒስታን ዜጎች በነፃ ለቃ ወደ ሃገራቸዉ መላክዋን ዋሽንግተን የሚገኘዉ የዩኤስ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

እስረኞቹ በጎርጎረሳዊዉ 2002 እና 2003 , በሀገራቸዉ ዉስጥ በአሸባሪነት ተጠርጥረዉ ነዉ ለጓንታናሞ እስር ቤት የበቁት። ቀደም ሲል ስድስት የጓንታናሞ እስረኞች ተለቀዉ ለኡራጓይ መሰጠታቸዉ ይታወቃል። ዛሬ መለቀቃቸዉ ከተሰማዉ አራት የጓንታናሞ እስረኞች ሌላ በጓንታናሞ 132 እስረኞች እንደሚገኙ የአሜሪካዉ የመከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን አስታዉቋል።

በጎርጎረሳዊዉ መስከረም 11 ቀን 2001 , ዩኤስ አሜሪካ ዉስጥ ከባድ የአሸባሪዎች ጥቃት ከደረሰ በኋላ ከተለያዩ የዓለም አገራት በአሸባሪነት የተጠረጠሩ 779 ሰዎች ጓንታናሞ በሚኘዉ የአሜሪካ የባህር ኃይል ጦር ሰፈር ለእስር በቅተዋል። ከነዚህ እስረኞች መካከል አብዛኞቹ እስካሁን ክስም ሆነ ብይን አልተላለፈባቸዉም። ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ 2009 , የፕሬዚዳንትነትን ስልጣን እንደያዙ ኪዩባ ጓንታናሞ የሚገኘዉን እስር ቤት እዘጋለሁ ሲሉ ቃል ገብተዉ ነበር። ነገር ግን ኦባማ ይህን ቃላቸዉን እስካሁን ባለመጠበቃቸዉ ከአሜሪካዉ ምክር ቤት፤ ከፍትህ ጉዳይ ቢሮና ከብዙኃን መገናኛ ትልቅ ነቀፊታ ደርሶባቸዋል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ