አምነስቲ ኢንተርናሽናልና የኮምፒዩተር ስለላ መከላከያው «ዲቴክት» | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 26.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

አምነስቲ ኢንተርናሽናልና የኮምፒዩተር ስለላ መከላከያው «ዲቴክት»

ምግብ ማግኘት ፍጹም መሠረታዊ ሰብአዊ መብት ነው፤ መብቱን የሚገነዘብለት ፣ መብቱን የሚያከብርለት --ኖረም -አልኖረ! የገንዘብ አቅም ላለው ደግሞ፣ በኢንተርኔት አገልግሎት መሥመር መጠቀምም መሠረታዊ ሰብአዊ መብት ነው። ይህ አገልግሎት ፍጹም

Multimedia Auge Cyberwar

ተፈላጊ መሆኑንም ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ዋስትና ጉዳይ ተመልካች የምርምር ማዕከላት ፤ በወተርሉ፣ ኦንታሪዮ፣ ካናዳና በፓሪስ ፈረንሳይ የሚገኙት፤ Centre for International Governance Innovation(CIGI) እና Ipsos ፣ በዓለም ዙሪያ፣ በ 24 አገሮች ፣ ካለፈው መስከረም 27 እስከ ኅዳር 3 ቀን 2007 ዓ ,ም ባካሄዱት የሕዝብ አስተያየት መመዘኛ መጠይቅ ላይ አረጋግጠዋል።

በደቡብ አፍሪቃ ፤ በኬንያ፤ ቱኒሲያ፣ ግብፅ ፣ናይጀሪያ ፤ አውስትሬሊያ፤ ብራዚል ፤ ካናዳ ፣ ቻይና፤ ፈረንሳይ ፤ ጀርመን፤ ብሪታንያ፣ ሆንግ ኮንግ ፤ ሕንድ፣ ኢንዶኔሺያ ፤ ኢጣልያ፤ ጃፓን፤ ሜክሲኮ፣ ፓኪስታን ፣ ፖላንድ፣ ደቡብ ኮሪያ፤ ስዊድን ፣ ቱርክና ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በአጠቃላይ 23,376 ሰዎች ነበሩ የተጠየቁት። ታዲያ 83 ከመቶው፤ መጠቀም እስከታቻለ ድረስ የኢንተርኔት አገልግሎት ፣መሠረታዊ የሰብአዊ መብት መሆኑ ሊሠመርበት እንደሚገባ ነው የተናገሩት።በሰፊው ድምፅ የሰጡትም በአምባገነን አገዛዝ ዘመናት የማቀቁ አገሮች ተወላጆች ናቸው። ምሳሌ፤ ግብፅ ፤ ናይጀሪያ፤ ኢንዶኔሺያና ቱኒሲያ። ከተጠየቁት ቻይናውያን መካከል እንዲያውም 90 ከመቶው፣ ኢንተርኔት፣ መሠረታዊ ሰብአዊ መብት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።

በላቲን አሜሪካ ፤ በመካከለኛው ምሥራቅና በአፍሪቃ፤ 46 ከመቶው በኢንተርኔት አጠቃቀም ረገድ የግለሰባዊ ነጻነትና መብት ጉዳይእጅግ እንደሚያሳስባቸው ነው የገለጡት። አውሮፓውያን፣ 18 ከመቶ ሰሜን አሜሪካውያኑም 23 ከመቶ ብቻ ናቸው ይህ አሳሳቢ ሆኖ የሚታያቸው። በኢንተርኔት የሚተላለፍ መረጃ የተጠበቀ ስለመሆኑ የሚያምኑ ጀርመናውያን 15 ከመቶ ብቻ ናቸው። ናይጀሪያውያን--58 ከመቶ ።

64 ከመቶውም ወይም 2/3ኛዎቹ ፤ ከአንድ ዓመት ወዲህ የ«ኦንላይን » አገልግሎት የግል ሰነድም ሆነ ምሥጢር የሚጠበቅበት ሁኔታ ይበልጥ እንዳሳሰባቸው ሳይጠቅሱ አላለፉም። 91 % የኢንተርኔት ተጠቃሚዎቹ እንዲያውም፤ ኢንተርኔት ጠቀሚ መረጃ ለማግኘት ፣ የሳይንስ ዕውቀትም ለመገብዬት ወሳኝነት እንዳለውና ለወደፊት እጅግ ተፈላጊ መሆኑን ነው ያስታወቁት። 87 ከመቶው ፣ ኢንተርኔት ለግላዊ ደስታና አዝናኝነት ወሳኝነት እንዳለው ጠቁመዋል።

የአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ፣ በተለይ በተንቀሳቃሽ ስልክ (ሞባይል) የመጠቀም ዝንባሌውና ፍላጎቱ እጅግ እየጨመረ ፤ በተለይ እ ጎ አ እስከ 2020 975 ሚሊዮን አፍሪቃውያን የዚሁ ሥነ ቴክኒክ ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑ እየተነገረ ባለበት ወቅት ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት የማግኘት መብትም ፣«መሠረታዊ ሰብአዊ መብት ነው» እየተባለ በሚነገርበት ባሁኑ ዘመን፣ ታዲያ ፤ የኢንተርኔት አገልግሎት፣ ለሰብአዊ መብት ረገጣ፤ በተለይም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችንና ጋዜጠኞችን ተግባር በስለላ ለመከታተል የሚያውሉ መንግሥታት መኖራቸው ባለፉት ወራት በሰፊው መነገሩም፣ መጋለጡም የሚታወስ ነው። አንዳንድ በሰብአዊ መብት ጥሰት የታወቁ አገሮች፤ ፤ የሰውን ልጅ መሠረታዊ መብት ረግጠው፣ በሰፊ የገንዘብ ወጪ የኢንተርኔት የስለላ መሣሪያ በመግዛት ክትትል ለማድረግ እንደሚጥሩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከማጋለጥ የቦዘኑበት ጊዜ የለም ። ማጋለጥ ብቻ ሳይሆን ፣ ለመቋቋም ከተባባሪዎች ጋር ጥረት ማድረጋቸው አልቀረም። ስለተቃጡ አደጋዎች ሲወሳ ጎልቶ የሚጠቀሰው ፤ FinFisher ወይም FinSpy የተሰኘው የኮምፒዩተሮችና የእጅ ስልኮች፣ እንዲሁም የንዑስ ሰነድ ማስቀመጫ ዲስክ(ፍላሽ ዲስከ ወይም USB) የግል መረጃዎችንና ሰነዶችን የሚሠረሥረውም ሆነ የሚሠርቀው መሣሪያ ነው። የሚዘጋጀውም «ጋማ» በተሰኘው፣ የብሪታንያና የጀርመን ንብረት በሆነው ኩባንያ ነው። የጋማ ዋና ማዕከል በደቡባዊው ጀርመን የምትገኘው ታዋቂዋ ከተማ ሙዩኒክ ናት። ጋማ ኢንተርሽናል፤ ሐሰት እያለ ቢያስተባብልም፤ ቢክድምሰብአዊ መበመርገጥ ለታወቁ መንግሥታትም ይህን የስለላ መሣሪያውን መሸጡ ተደርሶታል። ለምሳሌንም ያህል የባህሬይን ፣ የግብፅና የኢትዮጵያን የመሳሰሉ መንግሥታት ይጠቀሳሉ። በዩናይትድ ስቴትስና በብሪታንያ ኗሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ፣ «ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል» የተሰኘው የብሪታንያው ድርጅት ጭምር ተቃውሞ ማሰማታቸው አይዘነጋም።

የመፍቀሬ ዴሞክራሲ አባላት የሆኑ 3 የባሕሬይን ተወላጆች የሆኑ ዐረቦች፤ ፣ ምንም እንኳ ካገር ርቀው በባሪታንያ የሚኖሩ ቢሆኑም፤ የአገራቸው መንግሥት «ፊን ፊሸር ወይም ፊንስፓይ በተሰኘው የስለላ ክትትል እንደሚደረግባቸው ባለፈው ወር ነበረ በይፋ ያጋለጡት።

ታዲያ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጥንቃቄ በማድረግ ፤ ኮምፒዩተሮቻቸው የስለላ ሰለባዎች ሆነዋል አልሆኑም እንዲቆጣጠሩ፣ ጥቃት ሲሰነዘርም፤ ይከላከሉ ዘንድ የሚያስችል«ዲቴክት» የተሰኘ መሳሪያ አቅርቤአለሁ ሲል ባለፈው ሳምንት ኀሙስ ማብሠሩ ይታወሳል። መከላከያው መሣሪያ (ሶፍትዌር) ፣ ከፍተኛ የሥነ ቴክኒክ ዕውቀት ብቻ ሳይሆን ለሰብአዊ መብት መጠበቅ ከቆሙ ሰዎች ጋር በመተባበር የተሠራ ነው። AI ፣ «ዲጊታለ ጌዜልሻፍት» ከተሰኘው የጀርመን ፤ «ኤሌክትሮኒክ ፍሮንቲዬር ፋውንዴሽን ከተሰኘው የዩናይትድ ስቴትስ እንዲሁም ፤ «ፕራይቨሲ ኢንተርናሽናል» ከተባለው የብሪታንያ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው፣ የታወቁ የስለላ ሶፍትዌሮችን ለይቶ በማወቅ የሚከላከለውን «ዲቴክት» የተሰኘውን ሶፍትዌር በነጻ አገልግሎት እንዲሰጥ ሥራ ላይ ያዋለው። ፣ማሬክ ማርዥንስኪ የተባሉት የአምነስቲ ባልደረባ ፣«መንግሥታት ፤ አደገኛና ረቂቅ የስለላ ሥነ ቴክኒክን በስፋት በመጠቀም ላይ ናቸው። በሥለላ መሣሪያ አማካኝነት፤ የሰብአዊ መብት ታሟጋቾችንና የጋዜጠኞችን የግል ኢ ሜይል ደብዳቤዎች ማንበብ፤ የሥራ እንሥቃሴዎች ከሩቅ መከታተል ፤ የኮምፒዩተሮቻቸው ካሜራ ወይም ማይክሮፎን ሥራውን በመጀመር በምሥጢር የሥራ እንቅሥቃሴአቸውን እንዲቀርጽ ማድረግም እንደሚያስችላቸው መገንዘብ መቻሉንም የአምነስቲው ባልደረባ ያስረዱት። «ዲቴክት» ተጠቃሚዎቹ እንበል የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ፤ የመከላከያ እርምጃ እንዲወስዱ የሚያስጠነቅቅ መሣሪያ ነው። የአምነስቲ ድረ-ገጽ ራሱ የ«ዲቴክት» ግልባጭ የማስጠንቀቂያ ማስታወሻ አለው፤ አደጋ!! አንድ አደጋ የሚደቅን የስለላ እንቅሥቃሤ መከሠቱን አረጋግጬአለሁ።!

ይህን ኮምፒዩተር ከኤሌክትሪክ ማግኛ ሶኬት ያላቅቁት እንደገናም ከኢንተርኔት ጋር ወይም ከውጭ ሌላ መሣሪያ ጋር አያገናኙት! ርዳታ ይጠይቁ!! የሚል ነው። ማሳሰቢያው።

ዲቴክት በአሁኑ ጊዜ በ 6 ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ፤ከኢንተርኔት ድረ ገጽ በነጻ ተገልብጦ ለተፈለገው ጥቅም እንደሚውል AI አስታውቋል ። ቋንቋዎቹም፤ አማርኛ ፤ ዐረብኛ እንግሊዝኛ ፣ ጀርመንኛ ፤ ጣልያንኛና እስፓኝኛ ናቸው።

የAI ባልደረባ ታንያ ዖ’ካሮል እንዳስገነዘቡት፤ «ዲቴክት» የተቃጣ ስለላን በመጠቆም ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፤ ያን ማድረግ ሳይችል ቢቀር እንኳ አደጋ አይኖርም ብሎ ፍጹም መተማመን አይቻልም።

«ዲቴክት» ን ለማስተዋወቅ እንዘጋጅ በነበረበት ወቅት በመገናኛ ረገድ ስላለው አሳሳቢ ሁኔታ በጥብቅ ማሰብ ማሰላሰላችን አልቀረም። ከሰብአዊ መብግታ ታጋዮች ጋር ግንኙነት ፈጥረን ስንመካከር ፣ ዲቴክት አንድ አደጋን ጠቋሚ መሣሪያ እንጂ ቤዛ እንዳልሆነ ነው ያስረዳን። መንግሥታት የሚያደርጉት ክትትልና ቁጥጥር እጅግ እየተስፋፋ መምጣቱ ፣ የስጋቱም መጠን መጨመሩ ግልጽ ነው። እዚህ ላይ ማንቃት የምንፈልገው ፍቱን የሆነ መድኃኒት ተገኘ ብለን ማስተማመኛ መስጠት እንደማንችል ነው። ዋናው ነገር መሣሪያው አዳዲስ ሥጋቶች መደቀናቸውን ይጠቁማል። ይሁን እንጂ ከጉዳት ፍጹም ነጻ መሆን ተችሏል ማለት አይደለም። ሌላው የምናደርገው ሰዎች በ «ኦንላይን» አማካኝነት መመሪያው ቀርቦላቸው ይበልጥ ዕውቀቱ እንዲኖራቸውና የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ ጥቃቱን እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ፣ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ይወስዱ ዘንድ ማገዝ ነው። »

በመገናኛ ሥነ ቴክኒክ መራቀቁ ያስገኘውን ሰፊ ጥቅም ያክል፣ ጉዳት ወይም ደንቃራ የፈጠረበት ተያያዥ ፈተናም የዚያኑ ያክል ነው። የግል ኮምፒዩተሮችን ተግባር የሚያሠነካክሉ፤ ሰነዶችን ፤ መረጃዎችን የሚሠርቁ የተለያዩ ረቂቅ መሣሪያዎች አሉ። በካሊፎርኒያ ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ዋና ማዕከሉ የሆነው «ሳይማንቲክ» የተባለው ሶፍትዌር ሠሪ የአክሲዮን ድርጅት ባልደረባ ካንዲድ ቩዑስት ለዶቸ ቨለ እንዳብራሩት ፣ ኩባንያቸው፤ እ ጎ አ, ከ 2008 ዓ ም አንስቶ መረጃዎችን ሲሠረሥር ፣ሲሰርቅ የነበረ እኩይ የኮምፒዩተር ተኀዋሲ ፣ ሶፍትዌር (ማልዌር-ማሊሸስ ሶፍትዌር) ተከታትሎም ሆነ ፈልጎ ማግኘት ችሏል።

በአሁኑ ዘመን በረቀቀ የኮምፒዩተር አሠራር ፤ ድብቅ፤ አድፋጭ አደጋ አድራሺዎች (ትሮጃንስ) ና የኮምፒዩተር ተኀዋስያን መኖራቸው የታወቀ ነው። ሬጊን የተባለውን ምን የተለየ የሚያደርገው ሁኔታ አለ? ለቩዑስት የቀረበላቸው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር።

«ይህን የሥለላ መሣሪያ ፣ ሬጊንን በእርግጥ የተለየ የሚያደርገው የረቀቀና (በአራዳዎች ቋንቋ-«ሸዋጅ» በመሆኑ ነው። እጅግ ብርቅ መሣሪያ ነው። እንዲህ ዓይነት የረቀቀ መሣሪያ የሚያጋጥመን ምናልባት በዓመት ወይም በ 2 ዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው።»

Computervirus Virenalarm

የሬጊን ዓላማ ምንድን ነው እንዴት ነው የሚሠራ?

«ፍጹም ግልፅ ነው። ሬጊን ሰፊውን ሕዝብ እንዲሠልል የተዘጋጀ መሣሪያ ነው። ዋና ተግባሩም፤ ከተለያዩ ዒላማዎች መረጃዎችን መሰብሰብ ፤ ማግኘት ነው። መረጃ ሲባል አንዳንድ ፣ በአንድ ማሺን የተጠራቀሙ ሰነዶች የስልክ አውታሮችን በመሠርሠር፤ የተለያዩ መረጃዎችን ፣ የስልክ ጭውውቶችን መጥለፍ --የተለመደ የሰላዮችን የመሰለ ተግባር የሚፈጽም ነው። እነማን ከአነማን ጋር ተደዋወሉ? እንዲህ ዓይነቱን ሁሉ የሚከታተል ነው።»

እንዲህ ዓይነቱን ረቂቅ መሣሪያ ማን ሊሠራው ይችላል?

«እርግጥ ነው ረቂቅነቱን ሲያጤኑት፤ በእንዲያ ያለ ሁኔታ ሠርቶ ለማቅረብ፣ የተደረገውንም ጥረት ሲያስቡት፤ ዒላማ የተደረጉት አገሮችም ሩሲያና ስዑዲ ዐረቢያ መሆናቸውን እንደመገንዘባችን መጠን፤ መሣሪያው በመንግሥታት የተቀነባበረ የስለላ መሣሪያ መሆኑን ነው የሚጠቁመን። እንዲህ ዓይነት መሣሪያ ሠርተው ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉ ደግሞ ፣ በዓለም ውስጥ ጥቂት ሃገራት ናቸው።»

ኮምፑዩተሬ ፤ በእኩይ የኮምፒዩተር ተኀዋሲ ተልእኮ አለመበላሸቱን እንዴት ዐውቃለሁ?እንዴት ነው መከላከል የምችለው?

b

«ባቀረብነው ዘገባ፣ እንዴት ለይቶ ማወቅ እንደሚቻል፤ ዝርዝር ቴክኒካዊ አሠራሮችን ጠቁመናል። በአርግጥ በ«ሳይማንቲክ» መሣሪያ እ ጎ አ ካለፈው ዓመት ታኅሳስ 2013 ዓ ም አንስቶመከላከያውን አስቀምጠናል። በእኛ «ሶፍትዌር» የሚገለገሉ ደንበኞቻችን የኮምፒዩተር ጥቃት እንዳይደርስባቸው መከላከያውን አቅርበንላቸዋል።--ዘመናዊ የሆነውን።»

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic