አምስት ፓርቲዎች ሊዋሐዱ ነው | ኢትዮጵያ | DW | 13.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

አምስት ፓርቲዎች ሊዋሐዱ ነው

አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊዋሐዱ መሆኑን አስታወቁ። በመጪው ሐሙስ ይፈፀማል በተባለው ውሕደት ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እንደሚቋቋም በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል። አቶ ተሻለ ሰብሮ የሚመሩት የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ በውኅደቱ ተስማምቶ ሒደቱን ቢጀምርም በስተመጨረሻ ግን ኢራፓና ሌሎች ሁለት ፓርቲዎች በውህደቱ አልተገኙም።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:06

አምስት ፓርቲዎች ሊዋሐዱ ነው

አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊዋሐዱ መሆኑን አስታወቁ። በመጪው ሐሙስ ይፈፀማል በተባለው ውሕደት ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እንደሚቋቋም በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል። ተዋሕደናል ያሉት ቱሳ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት፣ ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ፣ የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት እና ደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮከቦች ቅንጅት ናቸው። አቶ ተሻለ ሰብሮ የሚመሩት የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ በውኅደቱ ተስማምቶ ሒደቱን ቢጀምርም በስተመጨረሻ አፈንግጧል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች