1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሜሪካና የኢትዮጵያን ግንኙነት የማሻሻል ጥረት

ዓርብ፣ ግንቦት 27 2013

ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ባነሳቻቸው ጉዳዮች ላይ በማተኮር የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ መመለስ እንደሚገባ ተገለፀ። አሜሪካ የጣለችውን ማዕቀብ እንድታነሳም ለሕዝብ ተወካዮችና ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የስልክ ጥሪ ዘመቻ መጀመሩ ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/3uQsS
Äthiopien Äthio-Amerikanische Bürger Demonstranten in Addis Abeba vor USA Botschaft
ምስል Seyoum Getu/DW

«ለአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት አባላት የስልክ ጥሪ ዘመቻም ተጀምሯል»

ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ባነሳቻቸው ጉዳዮች ላይ በማተኮር የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ መመለስ እንደሚገባ ተገለፀ። ዶይቸ ቬለ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው በጆርጂያ የአፍሪካውያን ማኅበር ምክትል ኘሬዚዳንት ዶክተር ተጋ ሊንዳዶ የሁለቱን ሃገራት ውዝግብ ከሚያባብሱ ተግባራት መቆጠብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በሌላ በኩል የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ይዞታል ያለውን የተሳሳተ አቋም ለማስቀየርና የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ለአሜሪካ ሕዝብ ተወካዮችና ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የስልክ ጥሪ ዘመቻ መጀመሩን ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ድምፅ አስታውቋል::

 ታሪኩ ኃይሉ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ