አማፂው ታሚል ታይገር በስተመጨረሻ እጅ ሰጠ | ዓለም | DW | 18.05.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

አማፂው ታሚል ታይገር በስተመጨረሻ እጅ ሰጠ

የአውሮጳ ህብረት በበኩሉ በውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባው፤ በጦርነቱ የተፈፀመውን የሠብዓዊ መብት ጥሰት ለማጣራት በስሪላንካ በአስቸኳይ ነፃ አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ጠይቋል። በሶስት አስርት ዓመታቱ የስሪላንካ ግጭት ወደ ሰባ ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸው ይጠቀሳል።

የታሚል ስደተኞች-ስሪላንካ

የታሚል ስደተኞች- ስሪላንካ

በሰሜን የስሪላንካ ግዛት የሚንቀሳቀሰው የታሚል ታይገር አማፂ ቡድን፤ ከሶስት አስርት ዓመታት የርስ በርስ ጦርነት በኋላ መደምሰሱ ተገለፀ። የመጨረሻዎቹ አማፂያን ይንቀሳቀሱበት የነበረውን የሰሜን ግዛትም የመንግስት ወታደሮች ሙሉ በሙሉ እንደተቆጣጠሩት የሲሪላንካ ጦር ሠራዊት አዛዥ Sarath Fonseka ዛሬ መግለፃቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። የታሚል ታይገር አማፂያን ወደ ሃምሳ ሺህ የሚጠጉ ሠላማዊ ሰዎችን ለሳምንታት ከበው በመያዝ የጦርነቱ ሠብዓዊ ጋሻ የማድረግ ኢ-ሠብዓዊነትን ፈፅመዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ሰሞኑን መኮነኑም ይታወቃል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ