አማራጩ የኖቤል ድርጅትና ዓላማው፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 15.09.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

አማራጩ የኖቤል ድርጅትና ዓላማው፣

በታዋቂው የሥነ-ቅመማ ሊቅና ፈልሳፊ ፤ አልፍረድ ኖበል ስም፤ ካለፈው ምዕተ ዓመት መግቢያ አካባቢ አንስቶ ፤ በያመቱ በመጸው በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች፤

default

የ Right livlihood Award መሥራች ፤ ያኮብ ፎን ዑክስኩዑል፣

ህክምና ፤ ኤኮኖሚ፤ እንዲሁም ሥነ -ጽሑፍና ሰላም የውድድር አሸናፊዎች ስም እንደሚገለጥና ታኅሳስ 1 ቀን ሽልማት እንደሚሰጥ የታወቀ ነው።

ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ ፣ ፤ በእስዊድናዊ -ጀርመናዊው ቴምብር ሰብሳቢ፣ ጋዜጠኛና ቀድሞ የአውሮፓ ፓርላማ አባል በነበሩት፣ ያኮብ ፎን ዑክስኩዑል ስም፣ ግለሰቡ ካፈሩት ንብረት፣ አንድ ሚሊዮን ዶላር መድበው ፣ እ ጎ አ ከ 1980 ዓ ም አንስቶ በያመቱ ለውድድር አሸናፊ ግለሰቦችና ድርጅቶች 50 ሺ ዩውሮ ሽልማት እንዲሰጥ ማድረግ ከጀመሩ ዘንድሮ 30 ዓመት ይሆናል ማለት ነው።

Right Livlihood Awarad በሚል ስያሜ የሚሰጠው ሽልማት ትኩረት ያደረገው በ 3 ዐበይት ዘርፎች፣ በተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ፤ በልማትና በሰብአዊ መብቶች ላይ ነው። ያኮብ ዑክስኩዑል፣ ለምን ይሆን ለተፈጥሮ አካባቢ ላቅ ያለ ግምት የሰጡ? መልስ አላቸው።

«የተፈጥሮ አካባቢ ሽልማት የማይሰጥበት ምን ምክንያት አለ? ለተፈጥሮ አካባቢ ግንዛቤ እንዲኖረን ማድረግና የምኖርበትን አካባቢ መንከባከብ እንዴት አያስፈልግም ! በእስዊድን እንደማደጌ መጠን የኖበል ሽልማት ማግኘት ለአንድ ሰው በዓለም ዙሪያ የቱን ያህል እንዲተኮረበት የሚያደርግ መሆኑን አውቃለሁ። በመሆኑም ፤ የኖቤል ሽልማት ሰጪ ኮሚቴ ይህን ጉዳይ በጥሞና እንዲመለከተው የሰበስብኩአቸውን ውድ ቴምብሮች በመሸጥ ለተፈጥሮ አካባቢ ሽልማት እንዲመደብ ለመስጠት ዝግጁ መሆኔን እስከመግለጽ ደርሼ ነበር።»

ይሁንና የኖቤል ኮሚቴ በማመሥገን የገንዘብ ሥጦታውን እንደማይቀበል ካስታወቃቸው በኋላ ነበረ፤ ፎን ዑክስኩዑል፤ ለትክክለኛ Right livelihood Award Foundation የተሰኘውን ድርጅት በማቋቋም፤ በዓለም ዙሪያ የታወቁ ግለሰቦችን በተለይ በዕለታዊ ተጨባጭ ተግባራት ላይ የተሠማሩትን በማሰበሰብ ውጤታማ የሆኑ ተግባራትን ላከናወኑ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ገምግመው ሽልማት ይሰጡ ዘንድ በዳኝነት የመደቧቸው።

«የእኛን ሽልማት የሚያገኙትም ሆኑ ሽልማት ሰጪዎቹ፤ ከድሆች ጋር ፤ በተጎሳቆሉ አካባቢዎች ፈንጠር ብለው በገጠርም የሚኖሩ ናቸው። »

እስካሁን ከ 58 አገሮች ለተውጣጡ ግለሰቦችና ድርጅቶች ሽልማት የሰጠው Right Livlihood Award ወይም የኖቤል አማራጩ ሽልማት ሰጪው ድርጅት ቦን ውስጥ ትናንት ጉባዔ የከፈተ ሲሆን፣ ከተለያዩ አገሮች ከመጡት መካከል ፣ ኢትዮጵያውያን ልዑካንም ይገኛሉ። ከመካከላቸው፤ በስብሰባ መካከል በተጣበበ ጊዜ ውስጥ በብዝኀ-ህይወት በአዝርእትና በመሳሰለው ሰፊ ምርምር ያደረጉትን የ «ጀኔቲክስ» ወይም የብዝኀ-ህይወት ሳይንቲስት ዶ/ር መላኩ ወረደን አነጋግረናል።--

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ