አለም የደቡብ ሱዳንን ነጻነት አወደሰ | ኢትዮጵያ | DW | 10.07.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

አለም የደቡብ ሱዳንን ነጻነት አወደሰ

በአፍሪቃ አህጉር በቆዳ ስፋትዋ ቀዳሚ ሆና የቆየችዉ ሱዳን፣ በደቡብ እና በሰሜን ተከፍላ፣ ደቡባዊዉ ሱዳን፣ ጁባን ዋና ከተማዉ በማድረግ ነጻነቱን አወጀ።

default

የአዲሱ መንግሥት የም/ቤት ፕሬዚደንት ጀምስ-ዋኒ-ኢጋ ጁባ ከተማ የደቡብ ሱዳንን ነጻነት በአበሰሩበት ስነ-ስርአት ላይ አስር ሽህ ህዝብ ተገኝቶአል፣ ሰላሳ የአፍሪቃ መንግስታት እና በርካታ አለማቀፍ እንግዶችም የዝግጅቱ ተካፋ ነበሩ። በስነ-ስርአቱ ላይ ከተገኙት እንግዶች መካከል በአለማቀፉ የጦር ወንጀል መርማሪ ፍርድ ቤት በጦር ወንጀለኝነት ለአስራት የሚፈልጉት የሰሜን ሱዳን ፕሪዝደንት ኦማር ሃሰን አልበሽር እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ጊ ሙን ይገኙበታል። የሰሜን ሱዳን ፕሪዝደንት ኦማር ሃሰን አልበሽር፣ በደቡብ ሱዳን ነጻነት ቀን ክብረ በአል ላይ በደቡብ ሱዳን ነዋሪ የሆኑት ወንድም እህቶቻችንን ለአዲሲትዋ ነጻ አገር መስረት እንኳን ደስ ያላችሁ! የደቡብ ህዝቦች ፍላጎት ይከበራል ሲሉ ንግግር ማድረጋቸዉ ተገልጾአል። ጀርመን ከሃምሳ አራተኛዋ አፍሪቃዊት አገር ከደቡብ ሱዳን ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንደምትጀምር ሲገለጽ፣ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የደቡብ ሱዳንን መሰረተ ልማት በመገንባቱ ረገድ አገራቸዉ እገዛ እንደምታደርግ ገልጸዋል።

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን