ንፁህ የመጠጥ ውሐን ለማዳረስ የተያዘው እቅድ አለመሳካቱ | ኢትዮጵያ | DW | 17.11.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ንፁህ የመጠጥ ውሐን ለማዳረስ የተያዘው እቅድ አለመሳካቱ

እስከ ዛሬ 3 ዓመት ድረስ በመላው ዓለም ንፁህ የመጠጥ እና የመፀዳጃ ውሐን ለማዳረስ የተያዘው እቅድ ግቡን ሊመታ እንደማይችል አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት አስታወቀ ።

default

ውሐ በጀሪካን የተሸከሙ ሴቶች

Water Aid የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት ሃላፊ ባርባራ ፎረስት እንደተናገሩት እስከ ዛሬ በተለይ በድሃ ሃገራት ውስጥ በዚህ ረገድ የታየ ለውጥ የለውም ። በሃላፊዋ ገለፃ መሠረት ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት ንፁህ የመጠጥና የመጸዳጃ ውሐን ለማዳረስ 200 ዓመታት ሊወስድ ይችላል ። ዝርዝሩን የለንደንዋ ወኪላችን ሃና ደምሴ አዘጋጅታዋለች ።

ሃና ደምሴ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዪ ለገሰ

Audios and videos on the topic