ንፁህ ዉሃ ለጤናማ ዓለም | ጤና እና አካባቢ | DW | 24.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ንፁህ ዉሃ ለጤናማ ዓለም

በዓለማችን ጦርነትና ሌሎች አደጋዎች ከሚያጠፉት የሰዉ ህይወት ይልቅ ንፅህናዉ ባልተጠበቀ ዉሃ ምክንያት የሚሞተዉ ህዝብ ቁጥር እንደሚበልጥ የተመድ አስታወቀ።

default

ዉሃ በሰሜን ወሎ

የዘንድሮዉ የዓለም የዉሃ ቀን ንፁህ ዉሃ ለጤናማ ዓለም የሚል መሪ ቃል ያነገበ ነዉ። የዛሬ አስር ዓመት የተመድ በአዉሮጳዉያኑ 2015ዓ,ም የንፁህ ዉሃ አርቦትን ለዓለም ህዝብ በማዳረስ የተሻሻለ የመፀዳጃ ስልት አገልግሎትንም እንዲሁ ለማስፋፋት አቅዶ ነበር። አሁን ያለዉን ነባራዊ እዉነታ የሚመለቱ ወገኖች በተለይ አንዳንድ አገራት ከዚህ ግብ የሚደርሱ አይመስሉም ማለት ጀምረዋል። በአንፃሩ በሰሜን አፍሪቃ፤ በምስራቅ እስያና በመሳሰሉት አካባቢዎች ደግሞ አዎንታዊ መሻሻሎች እየታዩ መሆኑ ተመልክቷል። በኢትዮጵያ የንፁህ ዉሃ አቅርቦትና የመፀዳጃና ንፅህና መጠበቂያ ስልቶች በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ?

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ