ኔቶ እና አዲሱ ዋና ጸሐፊው | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 02.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ኔቶ እና አዲሱ ዋና ጸሐፊው

የቀድሞ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚንስትር የንስ ስቶልትንበርግ አዲሱ የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ኪዳን ፣ ኔቶ ዋና ጸሐፊ በመሆን ትናንት በብራስልስ ስልጣናቸውን በይፋ ጀምረዋል። የ55 ዓመቱ ስቶልትንበርግ እአአ ከ2009 ዓም

Jens Stoltenberg neuer NATO Generalsekretär PK 01.10.2014

የኔቶ ዋና ጸሐፊ የንስ ስቶልትንበርግ

ወዲህ ኔቶን የመሩትን ተሰናባቹን ዴንማርካዊ ፎኽ ራስሙሰንን ነው የተኩት። አዲሱ የኔቶ ዋና ጸሐፊ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ ኪዳኑ በዩክሬይን ውዝግብ እና በሰበቡም ከሩስያ ጋር በተፈጠረው ልዩነት፣ በተለይም የኔቶ አባል የሆኑት የማዕከላይ እና ምሥራቅ አውሮጳ መንግሥታት ኔቶ በየሀገሮቻቸው ተጨማሪ ጦር እንዲያሠማራ ባቀረቡት ጥያቄ የተነሳ ትልቅ ፈታኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic