ኔታንያሁ በአዲስ አበባ | ኢትዮጵያ | DW | 07.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኔታንያሁ በአዲስ አበባ

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በማኅበራዊ በኤኮኖሚ እንዲሁም በሳይንስ እና ቴክኒዎሎጂ አብረዉ ለመስራት ተስማሙ። ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ትናንት ማምሻዉን አዲስ አበባ የገቡት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሃገራቸዉ በአፍሪቃ ኅብረት ዉስጥ የታዛቢነት ቦታ እንዲሰጣት ላቀረቡት ጥያቄ ኢትዮጵያ ድጋፍ መስጠቷ ተገለጸ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:21

እስራኤል እና ኢትዮጵያ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስት ቤንያሚን ኔታንያሁ 70 የሚሆኑ የንግድ ማኅበረሰብ አባላትን በመምራት ወደ ኢትዮጵያ የሄዱ ሲሆን፤ ኢትዮጵያዉያን በእስራኤል፤ እስራኤላዉያንም በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል። እስራኤል ከበርካታ የአፍሪቃ ሃገራት ጋር እጅግ በጠነከረ መልኩ እየሠራች እንደምትገኝ ያመላከቱት የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አጋር የሆነችዉ እስራኤልን እንዲህ አይነቱን ቦታ ለመከልከል ምንም ምክንያት እንደማይኖር መናገራቸዉን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ከአዲስ አበባ ዘግቦአል። በአፍሪቃ ኅብረት ዉስጥ አባል ያልሆኑ ሃገራት ተመሳሳይ ቦታ እንደሚሰጣቸዉ ዘገባዉ አክሎ አመልክቶአል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ናይሮቢን የጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እዝያ በነበሩበት ወቅት የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዉ እንደነበር ለማጣራት ከጋዜጠኛ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ የሚያዉቁት ነገር እንደሌለ መናገራቸዉንም አሶሽየትድ ፕሬስ ከአዲስ አበባ ዘግቦአል። ሚኒስትሩ በሃገር ዉስጥም ሆነ ከሃገር ዉጭ በፀጥታ ሃይላት ከፍተኛ ጥበቃ ሥር እንደሚንቀሳቀሱ ዘገባዉ አመልክቷል። ሚኒስትሩ በሃገር ዉስጥም ሆነ ከሃገር ዉጭ በፀጥታ ሃይላት ከፍተኛ ጥበቃ ስር እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል። የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic