ናይሮቢ ፍላይና ጣጣዋ | ጤና እና አካባቢ | DW | 16.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

ናይሮቢ ፍላይና ጣጣዋ

ወቅትን የጠበቁ የተለያዩ በሽታዎች ይከሰታሉ። ክረምት ሲታሰብ ቅዝቃዜ እና ዝናቡን አክሎ ጉንፋን ይፈራ ይሆናል እንጂ ቆዳ ላይ ችግር የሚያስከትል መዘዝ ስለመኖሩ ብዙም ሲነገር አይሰማም ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:16

ናይሮቢ ፍላይ

ከፌስ ቡክ ገጽ ላይ ያገኘናት መረጃ እንዲህ ትላለች፤ « ይህች የምታይዋት ነፍሳት ናይሮቢ ፍላይ ተብላ ነው የምትጠራው ምስሉ ላይ እንደምትታየው ሳይሆን ርዝመቷ እስከ አንድ ሴንቲ ሜትር በመሆኑ ቶሎ ላትለይ ትችላለች እንዲህ ክረምት ሲሆን ደሞ በብዛት ትራባለች፡፡ በፊት ወደ ጅማ አካባቢ ነበር ችግሩ ይታይ የነበረው ሰሞኑን ግን በመዲናችን በብዛት በመከሰቱ ቢያንስ በቀን አንድ ሰው ለህክምና እንደሚመጣ ነው የተነገረዉ፡፡ ማንኛውንም የተጋለጠ የሰውነት አካልን ከነካች ወዲያውኑ ነው ምልክት ማሳየት የሚጀምረው፡፡ የመጀመሪያ ቀን ቀላ ይላልበ ሁለተኛው ቀን ሽፍ ማለት ይጀምርና ውኃ ይይዛል ከዚያም ቆስላል። » እያለ ሊደረግ ስለሚገባዉ ጥንቃቄ ሳይቀር መጠነኛ ምክር ይለግሳል። ቢንቢ ወይንም ሌላ አነስተኛ ነፍሳት በእጅ ወይም በእግር አለያም ፊት ላይ ሲያርፉ ባሉበት አካል ላይ መትቶ የመግደል ልማድ አልፎ አልፎ ይስተዋላል። ግን ለክፉ የሚሰጣቸዉ አጋጣሚ ብዙም አይደለም። በተቃራኒዉ ሰዎች ሳያስተዉሉ አካላቸዉ ላይ እንዳለች ቢጨፈልቋት ናይሮቢ ፍላይ በመባል የምትታወቅ ጥንዚዛ መሰል አነስተኛ ፍጥረት ብትሞትም ከዉስጧ በሚወጣዉ መርዛማ ፈሳሽ የከፋ ጉዳት ታደርሳለች።

በእርግጥ ይህች የተባለች ፍጥረት ምንድናት? ከሰሞኑ ያጋጠመችስ ክስተት ብቻ ናት? ዶክተር ድጋፌ ፀጋዬ በአለርት የቆዳ እና የአባለዘር በሽታዎች ከፍተኛ ሃኪም ናቸዉ። ናይሮቢ ፍላይ የሚል ስያሜ የተሰጣት የሰዉ ቆዳ ላይ ችግር ልታስከትል የምትችል በራሪ ፍጥረት ሰሞኑን ብዙዎችን እንደተተናኮለች ሰምተናል፤ እንዴት ነዉ አልናቸዉ። ማብራሪያዉን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic