«ናኖ ቴክኖሎጂ» | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 11.02.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

«ናኖ ቴክኖሎጂ»

በላስ ቬጋስ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ፣ በባርሴሎና ፤ እስፓኝና በሃኖፈር ፣ ጀርመን በያመቱ ከጥር አንስቶ እስከ ሚያዝያ በየተራ ስለሚካሄድ የኤሌክትሮኒክስ ዐውደ ርእይ፣ ባለፈው ዝግጅታችን ስናወሳ ፣ ከሞላ ጎደል ስለ «ናኖ ቴክኖሎጂ» ጭምር መግለጻችን

ነበር። ቃላቱ ፣ ለአውሮፓም ሆነ ለሌሎች ቋንቋዎች ብዙ ቃላት ካዋሰው ከግሪክ ወይም ከጽርእ የተወሰዱ ናቸው። ናኖ--ናኖስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ ሲሆን ፤ ትንሽ ፣ኢምንት፣ ድንክ ማለት ነው ። ቴክነ (Techne)--ጥበብ ፤ ዘዴ ሲሆን፤ Logia የመሣሪያዎች፤ የማሺነሪ ስብሰብ፤ ማሻሻያና ፤ አጠቃቀም የሚለውን ትርጉም ይሰጣል ። በአሁኑ ዘመን ይበልጥ ትኩረት እየተደረገበት የመጣው ይህ ረቂቅ ሥነ ቴክኒክ-- ናኖ ቴክኖሎጂ ነው። ናኖ ቴክኖሎጂ በተጨባጭ ምንድን ነው ? እንዴት ሥራ ላይ ይውላል ፤ አፍሪቃ፤ ብሎም ኢትዮጵያ እንዴት የዚህ ሥነ ቴክኒክ ተጠቃሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ? በሥነ ቴክኒክ ጉዳዮች የሚተባበሩን፤ በትስዋኔ የቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ፕሮፌሰር ዶ/ር ማሞ ሙጨ ---

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic