«ኑሮን እንዳውቅ ወደ ኢትዮጵያ ተላኩ» | ባህል | DW | 21.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

«ኑሮን እንዳውቅ ወደ ኢትዮጵያ ተላኩ»

«በልጅነቴ አስቸጋሪ ልጅ ነበርኩ» ይላል። በዚህም የተነሳ ወጣቱ ከሚኖርበት ዮናይትድ እስቴትስ ለረዥም አመታት ወደ ኢትዮጵያ ተልኮ ነበር። ምትኩ ለገሠ ዛሬ የሃያ ስምንት ዓመት ወጣት ነው። ኢትዮጵያ ነው የተወለደው።

የሶስት አመት ልጅ ሳለ ከቤተሰቦቹ ጋ ወደ ዮናይትድ እስቴትስ ይሄዳል። ኑሮውም እዛው ይሆናል። ለቤተሰቦቹ ግን ምትኩ የሚመኙትን አይነት ልጅ አልሆነላቸውም። «በልጅነቴ አስቸጋሪ ልጅ ነበርኩ» ይላል ዛሬ።  4ኛ ክፍል እስኪደርስ ድረስ እንዲስተካከል ቤተሰቦቹ ብዙ ጣሩ። ችግሩን ማቃለል ግን አልቻሉም።  ስለሆነም ወደ ኢትዮጵያ ላኩት።
ከ12 ዓመታት የኢትዮጵያ ቆይታ በኋላ  ምትኩ  ተመልሶ በዮናይትድ እስቴትስ ኑሮውን ቀጥሏል።  ፀባዬን ለማሳመር ይህን ያህል ጊዜ ፈጅቶብኝ አይደለም ይላል። ምትኩ ሲመለስ ኑሮ በዮናይትድ እስቴትስ አልከበደውም ። የኢትዮጵያ ኑሮው ኃላፊነትንና ቁርጠኝነትን አስተምሮታል።
ታሪኩን አካፍሎናል። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic