ነፃ ጥበብን ፍለጋ - ኢትዮጵያ | ባህል | DW | 16.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ነፃ ጥበብን ፍለጋ - ኢትዮጵያ

«በዘመናዊ አቅድ ስዕል ራሱ ሐሳብ ነው። የአንድ ነገር ሁኔታ የአንድ ነገር ትርጉምና ስሜት ነው...። ዛሪ ስው ራሱን ብቻ መመልከት ትቶ ዓለም ከብዙ ርቀት ከብዙ በኩል ሲታይ ምን አይነት ስሜት አንደሚስጥ - ዓለማዊ ዘላለማዊ የሆነውን ነገር በመተርጎም - በዓይን የሚታይ፥ የቀለም፥ የመስመርና የቅርጽ ሙዚቃ ለመፍጠር ይጥራል።»

Atelierarbeit in Goethe Institut. und Ale School of fine Arts

ዴዛፍ አምስተኛ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ በሥነ-ጥበብ ዘርፍ በተደረገዉ ዉይይት ላይ

ሲል እዉቁ ኢትዮጵያዊ ሁለገብ ጥበበኛ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ሥነ-ጥበብን መተርጎሙን ጽሑፎች ያሳያሉ።

የእናት ፋንታ አባተ የሦስት ዓመት ልጅ ሳለች ስዕልን መዉደድ ብሎም መሳል መጀመሯን ትናገራለች። የሁለት ልጆች እናትዋ ሰዓሊ በጀርመን ሃንቡርግ በሚገኝ የሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት የማስተር ትምህርትዋን አጠናቃ፤ በዚሁ በሥነ-ጥበብ ዘርፍ ስራ ላይ ትገኛለች። እንዲህ እንደ አሁኑ ወቅት በዘርፉ እንብዛም ሴቶች ባልነበሩበት በከባዱ ጊዜ ይህን የጥበብ መንገድ ከትዉልድ ሀገርዋ ጎጃም ደብረማርቆስ መጀመርዋን የነገረችን የእናት ፋንታ፤ እዚህ ደረጃ ለመድረስ ከፍተኛ ጥረት ማድረግዋን ተናግራለች።

Yenatfenta Abate Vorbereitung der eignen Arbeit zur Ausstellung im Goethe Institute Addis Künstlerin aus Äthiopien

ሰዓሊ የእናትፋንታ አዲስ አበባ ጎተ የጀርመን የባህል ማዕከል ባዘጋጀችዉ አዉደ-ርዕይ ላይ


በርግጥ የእናትፋንታ ወደ ጀርመን እንደመጣች የቋንቋ ትምህርት ለመከታተል ወደ ሃይድልበርግ ከተማ ነበር ያቀናችዉ፤ በዝያ ቋንቋን ለሁለት ዓመት ከተከታተለች በኋላ ሃንቡርግ በሚገኝ የስነ-ጥበብ የከፍተኛ ተቋም ዉስጥ የስዕል ትምህርትዋን መከታተል ጀመረች። እንዳለመታደል ሆኖ በሐንቡርግም ትምህርቴን ስከታተልበት በነበረዉ ከፍተኛ ተቋም በክፍሌ ዉስጥ ብቸኛዋ አፍሪቃዊት ነበርኩም ስትል አጫዉታናለች።
በሀገራችን የነፃ የጥበብ አይነት የተጀመረ ስላልነበር በጎርጎረሳዉያኑ 1996 ዓ,ም «ነፃ ጥበብን ፍለጋ» በሚል አንድ መረሐ-ገብርን መጀመርዋን የምትገልፀዉ ሰዓሊ የእናትፋንታ፤ በየሁለት ዓመቱ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ወጣት ሰዓሊያን ጋር በመገናኘት እና ሃሳብን በመቀያየር ዘርፉን ለማሻሻል የተቻለ ጥረት መደረጉን ሳትag,ር አላለፈችም።
ሰዓሊ የእናትፋንታ ወደ ኢትዮጵያ ይዛዉ የሄደችዉን «ነፃ ጥበብን ፍለጋ» የተሰኘዉ መረሐ-ግብርን ምሳሌ በማድረግ ወጣት ሰዓልያን በቡድን የተለያየ ሥራዎችን መሥራት ጀምረዋል፤ ከዚህም መካከል « ነፃ የጥበብ መንደር» ተጠቃሽ ነዉ። በጀርመን በስዕል ትምህርት የከፍተኛ ደረጃ ትምህርትዋን ያጠናቀቀጥዉ ሰዓሊ የናት ፋንታ አባተ፤ ወጣት ሰዓልያን የተሰባሰቡበት « የስነ-ጥበብ ሥራዎችዋን በተለያዩ የጀርመን ከተሞች፤ በበርሊን በሚገኘዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲበተለያዩ ግዝያት በኢግዚቢሽን መልክ ለተመልካች አቅርባለች። ባለፈዉ ሰሞንም የኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች እና ምሩቃን ማህበር በጀርመን፤ በጀርመንኛ አፅህሮቱ «DÄSAV» ስድስተኛ ዓመታዊ ስብሰባዉን ባደረገበት ወቅት፤ በስነ-ጥበቡ ዘርፍ ተጋባዥ እንግዳ ሆና ቀርባ ነበር።

Atelierarbeit in Goethe Institut. und Ale School of fine Arts

ጎተ የጀርመን የባህል ማዕከል ዉስጥ ከወጣት ሰዓልያን ጋር የእዉቀት ልዉዉጥ


በሀገራችን የስነ-ጥበብ መፍለቅያ ናት በርካታ ያልተዳሰሱ ረቂቅ ስራዎች እንዳሉ የምትገልፀዉ እናት ፋንታ፤ ሀገር ዉስጥ ከሚገኙ ባህላዊም ሆኑ ስዕልን መሳል እንችላለን ብለን በማናስባቸዉ ነገሮች መስራት እንደሚቻል በቃለ-ምልልስዋ ገልፃለች። የኢትዮጵያ ሰዓልያን ወደ ማሕበረሰብ መገናኛ መንገድን በማግኘት እራሳቸዉን ሊያስተዋዉቁ የጥበቡን ዘርፍ ይበልጥ ተወዳጅ እንዲሆን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። ስዕልን ዉስጥ ሃሳብን መግለጫ ፤ ራስን ነጻ ማድረግያ፤ እምቅ ሃሳብን በህብረቀለም ለተመልካች ማቅረብያ ስትል ትርጉም የምትሰጠዉ ሰዓሊ የእናት ፋንታ አባተ፤ በስነ-ጥበቡ ዘርፍ በጀርመን እና በኢትዮጵያ መካከል ድልድይን ዘርግታ ባገኘቻቸዉ የነጻ ትምህርት እድሎች ሰዓልያን ወደ ጀርመን መጥተዉ የወራቶች የአሳሳል ስልጠናን እንዲያገኙ ጥረት አድርጋለች በቅርቡ ወጣት ሰዓልያን በዚሁ መረሐ-ግብር ስር ወደ ጀርመን ለመምጣት ዝግጅት ላይ መሆናቸዉ መዲና በርሊን ላይ በመነገር ላይ ነዉ። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic