ነፃ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል በጀርመን | ባህል | DW | 23.11.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

ነፃ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል በጀርመን

በየአመቱ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በውጭ ሀገር ነፃ ወይም ከፊል ነፃ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል እያገኙ ይሄዳሉ። እንደዚህ አይነት የትምህርት ዕድል ከሚሰጡ አገሮች አንዷ ጀርመን ናት።

ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ እውቀት መቅሰም የበርካታ ወጣቶች ህልም ነው። ከተለያዩ ሀገራት ተማሪዎች ስለሚያመለክቱ ነፃ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ወይንም «ስኮላርሺፕ» የማግኘቱ ሁኔታ ግን ውስን ነው። ጀርመን ዉስጥ ይህንን እድል ለአደጊ ሀገር ወጣት ተማሪዎች የሚሰጡ በርካታ ተቋማት ይገኛሉ፤ በዚህ ዝግጅት የሁለት ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎችን ተሞክሮ ቃኝተናል። ጌታነህ ዘውዱ፤ ተወልዶ ያደገው ባህር ዳር ከተማ ነው። የመጀመሪያ ዲግሪውን ካነኘ በኋላ በተማረበት መስክ ሲሰራ ቆይቶ ያለፈው አመት ነው ለድህረ ምረቃ ትምህርት ወደ ጀርመን ቦን ከተማ የመጣው። የከፍተኛ ትምህርት ዕድሉን እንዴት እንዳገኘ እና መሟላት ስለሚያስፈልጉት መስፈርቶች ገልፆልናል።


ማርኮ ኩን ፤የካቶሊካውያን የአካዴሚ የውጭ ተቋማት በምህፃሩ KAAD የአፍሪቃ ጉዳዮች ተጠሪ ናቸው። ስለ ተቋሙ አላማ ሲናገሩ፤ « እኛ የተለየ ትኩረት በምንሰጣቸው አዳጊ ሀገራት አቅም ግንባታ በኩል ድጋፍ ማድረግ እንፈልጋለን። ያም ማለት ተማሪዎቹ ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ወቅት የሀገራቸውን ሁኔታ እንዲያሻሽሉ እና ውጤት በሚያስገኝ መልኩ በተግባር እንዲያውሉ ነው።»

ለከፍተኛ የትምህርት እድል የሚያበቃ ዉጤት ያላቸዉ ተማሪዎች ለKAAD በኢሜል ማመልከቻቸዉን በመላክ መወዳደር እንደሚችሉ ነዉ ኩን የገለፁልን። ለመሆኑ ሙሉ በሙሉ ነፃ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ለማግኘት የሚችሉት ተማሪዎች የትኞቹ ናቸው?
« እኛጋ ለማመልከት አንድ ተማሪ የመጀመሪያ ዲግሪ ሊኖረዉ ይገባል። ስለዚህ የትምህርት ዕድል ያለን ለድህረ ምረቃ እና ለዶክትሬት ዲግሪ ነው። » ይላሉ ኩን።
KAAD ለአንድ ሀገር ወይንም አህጉር የሚሰጥ የተወሰነ ቁጥር ያለው የከፍተኛ ትምህርት እድል የለውም። በአመት ለምሳሌ ከኢትዮጵያ ከ5-7 አዲስ ተማሪዎች ይቀበላል። ለዚህም መመዘኛዎች አሉ።
« አመልካቾች በጣም ጥሩ የትምህርት ውጤት ሊኖራቸው ይገባል።

Plakat Deutsch-Türkischer Masterstudiengang

ለምሳሌ በኢትዮጵያ አሰራር ከ 3 እና 3,2 በላይ ውጤት ያላቸው መሆን አለባቸው። በዛ ላይ ደግሞ በቤተ ክርስትያናት ወይም በማህበራዊ አገልግሎት የሚሳተፉ መሆን ይኖርባቸዋል። ይህ ማለት በስራ መስኩ የተሳተፉ ይሁኑ ማለት ሳይሆን፤ በበጎ ፍቃደኝነት የሚያገለግሉ ማለቴ ነው። አባል መሆን ብቻውን በቂ አይደለም። ብቻ እኛ የምንቀበላቸው ሰዎች በአብዛኛው የአመራር ልምድ ያላቸውን ነው። »

የኔህይወት ብርሃኑ በአሁኑ ወቅት ጀርመን ዉስጥ በመማር ላይ ትገኛለች። በKAAD አማካኝነት ነዉ የትምህርት እድሉን ያገኘችዉ። የኔ ህይወት የካቶሊክ እምነት ተከታይ ናት። በተቋሙ ግን ተቀባይነት ለማግኘት ይህ ወሳኝ አይደለም ይላሉ ኩን። እንደውም እድሉን ካገኙት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያን ተማሪዎቻች የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መሆናቸውን ገልፀዉልናል።

ጀርመን ዉስጥ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ማግኘትን በሚመለከት የጠቀናቀረውን ዘገባ ማድመጥ ይችላሉ።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 23.11.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16ozl

ተዛማጅ ዘገባዎች

 • ቀን 23.11.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16ozl