ኃይሌ ሩትስ እና ሥራዎቹ | ባህል | DW | 24.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ኃይሌ ሩትስ እና ሥራዎቹ

ትዉልዱና እድገቱ አዲስ አበባ ከተማ ነዉ። በልጅነቱ ስዕልና እግር ኳስ የሚወድ ቢሆንም ከራስ ተፈሪያን ጀማይካዉያን ጓደኞቹ ጋር ያደምጣቸዉ የነበሩ የሬጌ ሙዚቃወችና መልዕክቶቻቸዉ ቀልቡን ወደ ሙዚቃዉ እንዲያዞር አድርጎታል።ቀስበቀስም ያደምጣቸዉ የነበሩ ሙዚቃወችን «ዜማላስታስ» ከተባለ የሙዚቃ ባንድ ጋር በመሆን በምሽት ክበቦች መጫወት ጀመረ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:19

«ኢትዮጵያ በሬጌ ሙዚቃ ያላትን ቦታ አልተጠቀመችበትም» ድምጻዊ ሀይሌ ሩትስ

የመዝገብ ስሙ ኃይለሚካኤል ጌትነት ይባላል። ብዙዎች የሚያውቁት ኃይሌ ሩትስ በተሰኘ የመድረክ ስሙ ነው። የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ ነው። «ችጌ »በሚል መጠሪያም የሬጌና የችክችካ ስልትን በአንድ ላይ ያጣመረ የሙዚቃ አልበም ለአድማጭ ጆሮ አብቅቷል። በረጅም ፀጉሩ እና ለየት ባለ አለባበሱ ቶሎ ከአይን ይገባል። በቅርቡ በስፔን አገር በተካሔደው ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ድግስ ላይ ተጋብዞ ሙዚቃዎቹን አቅርቧል። ከመዝናኛ ዝግጅት እንግዳችን ኃይሌ ሩትስ ጋር የነበረንን ቆይታ የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ። 

ፀሀይ ጫኔ

ሸዋዬ ለገሠ 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች