ቻይና፤ በ5000 ሜትርና ማራቶን የሴቶች ሩጫ ኢትዮጵያ አሸነፈች | ኢትዮጵያ | DW | 30.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ቻይና፤ በ5000 ሜትርና ማራቶን የሴቶች ሩጫ ኢትዮጵያ አሸነፈች

ኢትዮጵያውያት አትሌቶች ቤጂንግ ውስጥ በተካሄደው የሴቶች የአምስት ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር እሁድ ነሐሴ 24 ቀን፣ 2007 ዓ.ም. ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ተከታትለው በመግባት ድል አስመዘገቡ።

አትሌት አልማዝ አያና ተፎካካሪዎቿን በረዥም ርቀት በመቅደም 14 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ በሆነ ሰዓት ሩጫውን በአንደኝነት አጠናቃለች። ኹለተኛ ሰንበረ ተፈሪ፣ ሦስተኛ ደግሞ ገንዘቤ ዲባባ በመግባት የውድድሩ አሸናፊዎች ሆነዋል። ኢትዮጵያ ዛሬ ከዚህ ሩጫ በፊትም ሌላ አስደሳች ድል ተቀዳጅታለች።

በሴቶች የማራቶን ውድድር ማሬ ዲባባ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ 2ተኛውን ወርቅ አስመዝግባ ነበር። ላለፉት 9 ቀናት ቤጂንግ ውስጥ በተካሄደው እና ዛሬ የፍፃሜ ቀን በሆነው የአትሌቲክስ የዓለም ሻምፒዎና የሜዳሊያ የውጤት ሸንጠረዥ፤ 1ኛ ኬንያ 2ኛ ጃማይካ 3ኛ ዩናይትድ ስቴትስ፤ እንዲሁም ብሪታንያ 4ኛ ሲወጡ፤ ኢትዮጵያ በጠቅላላው 8 ሜዳሊያ በማግኘት 5ኛው ተርታ ላይ ተሰልፋለች። ጀርመን እንደ ኢትዮጵያ ስምንት ሜዳሊያ ኾኖም በኢትዮጵያ በአንድ ወርቅ ተበልጣ 7ኛ ደረጃን አግኝታለች።

ልደት አበበ

ማንተጋፍቶት ስለሺ