ቻርለስ ቴለር ለፍርድ ወደ ሃገን መዛወር | የጋዜጦች አምድ | DW | 21.06.2006
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

ቻርለስ ቴለር ለፍርድ ወደ ሃገን መዛወር

በጦር ወንጀለኝነት የተከሰሱት የቀድሞ የላይቤርያ መሪ ቻርልስ ቴለር ከተሸሸጉበት ከናይጄርያ ተይዘው ላይቤርያ ፍሪታውን ዉስጥ በእስር ላይ ከሁለት ወራት በላይ አስቆጥረዋልr

በትናንትናዉ ምሽት ደግሞ ቻርልስ ቴለር ኔዘርላንድ ወደ ሚገኘው የአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተዛዉረዋል።በአፍሪቃ በጦር ወንጀለኝነት በሙስና የሰበአዊ መብት በመርገጥ የሚታወቁት ጠንካራዉ ቻርልስ ቴለር ኒዘርላንድ አየር ጣብያ እንደደረሱ እጃቸዉን በሰንሰለት ታስረዉ እንደነበር፣ ከዚያም ከአዉሮፕላን ማረፍያዉ ሃያ ኬሎ ሜትር ርቆ ወደሚገኘዉ አለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች እስር ቤትም እንደተወሰዱ ታውቆአል። ይህ እስር ቤት ከዚህ ቀደም የቀድሞዉ የይጎዝላቪያ መሬ ኢስሎቮዳን ሚሎሶቪች ታስረዉበት እንደነበር ይታውቓል። የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ ኮፊ አናን የቻርልስ ወደ ጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት መዛወርን በደስታ ተቀብለዉታል «እርምጃዉ የዚህን መሰሉ ግፍ የፈጸመ ሳይቀጣ እንዳይቀር ታላቅ ምሳሌ ነዉ። ለላይቤሪያም መልሶ መቓቓም እና ሰላም የማግኘቱ ተግባር ላይ ድጋፍ ይሆናል» ሲሉ ገልፀዋል። TAZ የሚባለዉ የጀርመን እለታዊ ጋዜጣ አዘጋጅ በተለይም በአፍሬቃ ጉዳይ ላይ አዋቄ የሆኑት ለምን ቴለር በፍሪ ታዉን ፍርዳቸዉን እንደማያገኙ ሲገልፁ «ማንም ሰዉ ቴለር በላይቤሬያ ውስጥ እንዲታሰሩ ወይም ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚፈልግ የለም ብዙ ደጋፊዎቻቸዉ እናም አጎብዳጆቻቸዉ አሉ እና! በተለይ ደግሞ ለአገሪቱ ፀጥታ እና ደህንነት ሲባል። በተጨማሪ ቻርልስ ቴለር ለራሳቸዉ ደህንነት ሲሉ በሌላ ገለልተኛ አገር መታሰርን ይመርጣሉ»። የላይቤሪያ ባለስልጣናት ችሎቱ ወደ ሄግ እንዲዛወር የተባበሩት መንግስታትን ጠይቀዉ እንደነበር ይታወሳል። የምዕራብ አፍሬቃ አገራት መንግስታትም በአካባቢዉ ጠብ ይጫራል የሚል ስጋት አድሮባቸዉ እንደ ነበርም ታዉቆአል። ቻርልስ ቴለር እ.አ.አ 2003 በሰኔ ወር እስከ 2006 መጋቢት ወር ድረስ በናይጀርያ ጥገኝነት ጠይቀዉና ተሸሽገዉ እንደቆዩ ይታወቃል። ቴለር በላይቤሪያ አስራ አራት አመታት ለዘለቀዉ እና አራት መቶ ሺ ህዝቦች ህይወት ላሳጣዉ ጦርነት መነሻ ተጠያቄ እንደሆኑ ተገልፆአል። የቻርልስ ቴለር ኔዘርላንድ ወደ ሚገኘዉ አለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት መውረድ ወይም በፍሪታዉን ወስጥ ፍርዱን መቀበል ስላለዉ ልዩነት የጀርመኑ ጋዜጠኛ አስታያየት «በቴለር አገዛዝ ግፍ የደረሰባቸዉ ህዝቦች የቴለር በላይቤሪያ ፍርድ መቀበል ወይም በሃገን፣ ለዉጥ እንደማይሰጣቸዉ፣ ነገርግን ዋንኛዉ ትክክለኛ ፍርድ እና የእጃቸዉን ማግኘታቸ እንደሆነ ገልጸዋል።
በትናንትናዉ እለት የቻርልስ ቴለር ቤተሰቦች ቴለር ወደ ሃገን ለፍርድ ዕሮብ እንደሚሄዱ እንደተነገራቸዉ ነገርግን ማክሰኞ ምሽት መዛወራቸዉ ቻርልስ ተታለዋል ብለዋል። ቻርልስ በሃገኑ ፍርድቤት ምንአልባትም የእድሜ ልክ እስራት እንደሚፈረድባቸዉና ህይወታቸዉን በእስር በብሪታንያ ወስጥ እንደሚያሳልፉ ይገመታል።