ቸምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በአዲስ አበባ | የጋዜጦች አምድ | DW | 17.02.2005
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የጋዜጦች አምድ

ቸምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በአዲስ አበባ

የሀገር እና የውጭ ሀገር ባለተቋሞች የሚሠሩበትን ሁኔታ የማመቻቸት ዓላማ ይዞ የተነሣው ዘጠነኛው ቸምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ዛሬ በአዲስ አበባ ይከፈታል። ውድድርን ማስተካከል የሚል መርሕ የያዘውና አንድ ሣምንት የሚቆየውን ሠላሣ ሀገሮች የሚሳተፉበትን ዓለም አቀፍ ትርዒት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ ይጎበኘዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ወኪላችን ታደሰ እንግዳው የትርዒቱን አዘጋጂዎች በመጥቀስ አስታውቋል።