«ትግራይ እንዳለችው ካደረገች እርምጃ ይወሰድባታል»የብልጽግና ፓርቲ | ኢትዮጵያ | DW | 14.05.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

«ትግራይ እንዳለችው ካደረገች እርምጃ ይወሰድባታል»የብልጽግና ፓርቲ

የትግራይ ክልላዊ መንግስት በተናጥል ምርጫ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ፡፡ የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ አወሉ አብዲ የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ ምርጫ ማድረግ አይችልም ፤ ካደረገም መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:44

የትግራይ ክልል ምርጫውን በተናጥል እንደሚያካሂድ ገለጸ

የትግራይ ክልላዊ መንግስት በተናጥል ምርጫ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን ለክልሉ መንግስታዊ መገናኛ ብዙሐን በሰጡት መግለጫ በሀገር ደረጃ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም ተብሎ የሚደመደም ከሆነ ህዝብና የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያሳትፍ ምክክር መደረግ አለበት ብለዋል፡፡ የፌደራሉን መንግስት የሚመራው የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ አወሉ አብዲ በበኩላቸው የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ ምርጫ ማድረግ አይችልም ፤ ካደረገም መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። 

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች