ትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ «ደሚህት» መሪ ወቅታዊ ሁኔታ | ኢትዮጵያ | DW | 18.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ «ደሚህት» መሪ ወቅታዊ ሁኔታ

ትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ «ደሚህት»ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ከተዋጊዎቻቸዉ ጋር ከጥቂት ቀናት በፊት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:08

ትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ «ደሚህት» መሪ ወቅታዊ ሁኔታየኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣዉ መግለጫ ፣የኢትዮጵያ መንግስት የደሕንነት አካላት ከድተዉ ከገቡት ከደሚህት መሪ ጋር ዓመት ከዘለቀ ምስጢራዊ ድርድር በኋላ ወደ ሃገር ቤት እንዲመለሱ መደረጉን መግለፁ ይታወቃል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አዳማ ናቸው የተባሉትን የ(ደሚህት)ን መሪ አቶ ሞላ አስገዶምን ለማግኘት አዳማ ሄዶ ሊያገኛቸው አለመቻሉን ገልፆልናል።

በሌላ በኩል «የአርበኞች ግንቦት ሰባት» አመራር አባልና የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዶክተር ታደሰ ብሩ ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራስያዊ ንቅናቄ በምህፃሩ «ደሚህት» መሪና ጥቂት አባላቱ መክዳት ቀሪዉን ከፍተኛ ኃይል ያጠናክራል እንጂ አያዳክምም አሉ። ዶክተር ታደሰ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የደህንት መሪ ኢትዮጵያ ይዘው ገቡ የሚባለው ተዋጊ ቁጥር ቡድኑ ካለው ሠራዊት ቁጥር ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነው ብለዋል ።


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

መክብብ ሸዋ

አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic