ትውልደ ኢትዮጵያዊው ለሕዝብ እንደራሴነት በአሜሪካ | ዓለም | DW | 23.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ለሕዝብ እንደራሴነት በአሜሪካ

የሎሳንጄለስ አከባቢ (county) የምርጫ ግዛትን ለመወከል ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ ቴድ አለማየሁ ፉክክሩ ውስጥ መግባታቸውን ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል። አቶ ቴድ አለማየሁ ከ18 ዓመታት በፊት “የዩስ ዶክተሮች ለአፍሪቃ” የተባለ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በማቋቋም በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የጤና ክብካቤ ላይ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:55

ትውልደ-ኢትዮጵያዊው የሕዝብ እንደራሴ ተወዳዳሪ በሎስአንጀለስ

በመጪው ኅዳር ወር መጀመሪያ ላይ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የሥልጣን ዘመን አጋማሽ ምርጫ (Mid Term Election) ይካሄዳል። ይህ መርጫ በአሁኑ ሰዓት  የሪፐብሊካን ፓርቲ በሀገሪቱ የሕግ መወሰኛ እና የሕግ መምሪያ ምክር ቤቶች ላይ ያለውን የበላይነት ሊያሳጣው እንደሚችል የምርጫ ተንታኞች ይገልጻሉ። በሕግ መምሪያው ምክር ቤት ለምርጫው ክፍት ከሆኑት 435 መቀመጫዎች መካከል የካሊፎርኒያ ግዛት የሎሳንጄለስ አከባቢ (county) የምርጫ ግዛትን ለመወከል ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ ቴድ አለማየሁ ፉክክሩ ውስጥ መግባታቸውን ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል። አቶ ቴድ አለማየሁ ከ18 ዓመታት በፊት “የዩስ ዶክተሮች ለአፍሪቃ” የተባለ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በማቋቋም በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የጤና ክብካቤ ላይ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል። የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴ የአቶ ቴድ አለማየሁ የመርጫ ዘመቻን አስመልክቶ  ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic