ትኩረት በአፍሪካ | አፍሪቃ | DW | 17.04.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ትኩረት በአፍሪካ

የቻድ የምርጫ ኮሚሽን ባለፈው እሁድ የተካሔደውን ምርጫ ውጤት ይፋ ያደርጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። በምርጫው ላለፉት ሶስት አስርት አመታት ሥልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቤ እንደሚያሸንፉ የብዙዎች እምነት ነው። በምርጫው ያልተሳተፉት ሳሌሕ ኬብዛቦ የተባሉ ፖለቲከኛ ዴቤ ካሸነፉ ቻድን ለማስተዳደር አስቸጋሪ አደርጋታለሁ ሲሉ ዝተዋል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 14:46

ትኩረት በአፍሪካ

የቻድ የምርጫ ኮሚሽን ባለፈው እሁድ የተካሔደውን ምርጫ የመጀመሪያ ውጤት ይፋ ያደርጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። በምርጫው ላለፉት ሶስት አስርት አመታት ሥልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቤ እንደሚያሸንፉ የብዙዎች እምነት ነው። የ68 አመቱ ዴቤ በምርጫው ስድስት ተፎካካሪዎች ገጥመዋቸዋል። 
ከእነዚህ መካከል የቀድሞው ጠቅላይ ምኒስትር ፓሒሚ ፓዳክ አንዱ ናቸው። ይሁንና ከአምስት አመታት በፊት በተካሔደው ምርጫ የተሸነፉት ሳሌሕ ኬብዛቦን ጨምሮ በርካታ ዋና ዋና የሚባሉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በምርጫው ሳይሳተፉ ቀርተዋል። ሳሌሕ ኬብዛቦ እንዲያውም ዴቤ ምርጫውን ካሸነፉ ቻድን ለማስተዳደር አስቸጋሪ አደርጋታለሁ ሲሉ ዝተው ነበር። 

በዛሬው የትኩረት በአፍሪካ መሰናዶ እንዳልካቸው ፈቃደ የቻድን ምርጫ እና አፍሪካ የሚያስፈልጋት ዕርዳታ ሳይሆን ንግድ ነው የሚሉ ሁለት ርዕሰ ጉዳዮችን ይዳስሳል።

እንዳልካቸው ፈቃደ 
ታምራት ዲንሳ
 

Audios and videos on the topic