ትኩረት በአፍሪቃ | አፍሪቃ | DW | 29.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ትኩረት በአፍሪቃ

አፍሪቃ ውስጥ በታጠቁ አማፂያን እና ወታደሮች የመደፈር ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች በደልን አስመልክቶ ባከናወኑት ምግባር የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተወላጁ ዴኒስ ሙክዌጌ የ2014 የሳካሮቭ ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል። ዴኒስ ሙክዌጌ ማክሰኞ ኅዳር 17 ቀን፣ 2007 ዓም የአውሮጳ ምክር ቤት በመገኘት ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

በመሪዎቿ ብሎም ነፍጥ ባነሱ አማፂያን ተደጋጋሚ በደል የሚደርስባት አፍሪቃ ዛሬም በተለያዩ ስፍራዎቿ በደሉ አልተቋረጠም። የዛሬው ትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅት አፍሪቃ ውስጥ በወታደሮች እና በአማፂያን ስለሚደፈሩ ሴቶች የሚቃኝ ነው። በአስገድዶ መደፈር ጥቃት የደረሰባቸው ሰለባዎችን ለማከም ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፥ ቡካቩ ውስጥ የፓንዚ ሐኪም ቤትን መስርተው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያደረጉት የኮንጎው ተወላጅ ዴኒስ ሙክዌጌ ዘንድሮ የ2014 የሳካሮቭ ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል። በሕክምና ሙያ የተሰማሩት ዴኒስ ሙክዌጌ ሽትራስቡግ ከተማ በሚገኘው የአውሮጳ ህብረት ምክር ቤት በተዘጋጀላቸው የሽልማት ስነስርዓት ከህብረቱ የምክር ቤት ፕሬዚዳንት ማርቲን ሹልስ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል። የጋዜጦች አምድ ግጭት በሊቢያ፣ የማዳጋስካር ተስቦ፣ አምባገነን መሪዎች እና ባለቤቶቻቸው በአፍሪቃ የተሰኙ እና ሌሎች ዘገባዎችንም አካቷል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic