ትኩረት በአፍሪቃ | አፍሪቃ | DW | 25.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ትኩረት በአፍሪቃ

የሶማሊያ ምርጫ መዘግየት፣ አዲስ የአንድነት መንግስት የመሰረተችው ምዕራብ አፍሪቃዊት ሀገር ማሊ ፤ የመታሰቢያ ስነ ስርዓት ለማዕድን ቆፋሪዎች በደቡብ አፍሪቃ

በሙስና የተዘፈቀው እና ድጋፍ ያጣው የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ያለፈው ሰኞ ያከትማል ተብሎ ነበር።  በዕለቱም የታቀደዉየሶማሊያፕሬዝደንትምርጫ ሳይካሄድ ቀርቷል። በሶማሊያ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር የሚያካሂድ ተቋም ሃላፊ ጅብሪል አብዱል ምርጫው ከሚካሄድበት ቀን በፊት በሰጡት አስተያየት ምርጫው እንደሚዘገይ ነበር ለዶይቸ ቬለ የገለፁት።  የምክርቤትአባላትምርጫውየተቀመጡትንመስፈርቶችያሟላአልነበረም ነው ያሉት።

New Somali parliamentarians pray during an inauguration ceremony for members of Somalia's first parliament in 20 years in Mogadishu August 20, 2012, in this photograph released by the African Union-United Nations Information Support Team. Out of a total of 275 parliamentarians, 211 were sworn-in today at an open-air ceremony at Aden Abdulle International Airport in the Somali capital of Mogadishu. The Ministers of Parliament were selected by traditional elders and are scheduled to sit in the first session of parliament on August 21, where the process of selecting a speaker of parliament and a new president will begin after the current mandate of the UN-backed Transitional Federal Government (TFG) expired on Monday. REUTERS/Stuart Price/AU-UN IST PHOTO/Handout (SOMALIA - Tags: POLITICS RELIGION) THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS. FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS

የፓርላማ አባላት በፀሎት ላይ

ምክር ቤቱ ከሰኞ ጀምሮ ስብሰባ ጀምሯል። የመንግስት አመሰራረቱ የተወሰኑ ሳምንታት እንደሚፈጅ ነው የሚነገረው። መቼ ከሚለው ጥያቄ ውጪ አነጋጋሪው ማን ፕሬዚደንት ይሆናል የሚለው ነው።

ኤርፉርት ጀርመን በሚገኘዉ በማክስ-ፕላንክ የጥናት ተቋም የሶማሊያ ጉዳይ ተንታኝ ማርኩስ ሆነ እንደሚሉት መቼም ይሁን መቼ በፕረዚዳንትነት የሚመረጡት ሰው አሁንም በስልጣን ላይ የሚገኙ እንደሚሆን ነው። ሼክ ሸሪፍ አህመድ አንዱ እጩ ናቸው።

« ብዙ ምንጮች ስላሏቸው እድላቸው ሰፊ ነው። ሌላም ሊሆን ይችላል ውድድሩን የሚፈፅመው ይሁንና አዲስ ሰው ውድድሩን ይፈፅማል ብዬ አላስብም።  ምናልባት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሌሎች ባለፉት አመታት የተለዋወጡ በርካታ ሰዎች አሉ። ብቻ አዲስ ንፁህ የሆነ እና በዚህ በሙስና ወቀሳ ውስጥ ያልተካተተ ሰው ይመረጣል ብዬ አልገምትም። ይህ ቢሆን በጣም ነው የሚገርመኝ። ምናልባት ይህ አንድ ጥሩ ዜና ነበር። »

Somali President Sheikh Sharif Sheikh Ahmed arrives to mark the first year anniversary since the ouster of militant Al Shabaab fighters from the capital Mogadishu August 6, 2012. REUTERS/Omar Faruk (SOMALIA - Tags: CIVIL UNREST POLITICS ANNIVERSARY)

ሼክ ሸሪፍ አህመድ

ግን ምንም እንኳን አዲስ ሰው ቢመረጥ ተመልሶ ሙስና ከተዋኃዳቸው ጋ ስለሚቀላቀል የሶማሊያ የወደፊት እጣ ቀላል እንደማይሆን ነው።  ተንታኙ የገለፁት።

አዲሱ ህገ መንግስት በሸሪያ ህግ ላይ የተመረኮዘ ነው። ግብፅ፣ ቱርክ ፣ ካታር በሶማሊያ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያደርጉም ይነገራል። አገሪቷ ወግ አጥባቂ የሙስሊም አገር ከሆነች የምዕራቡን አገር የሚያሳስበው ጉዳይ ነው የሚል ትንታኔ ወቶ ነበር። በዚህ ላይ ማርኩስ ሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ፤

« እንደኔ አመለካከት ፤ ሙስና ውስጥ ሰርገው ያልገቡ እና እንብዛም በሰብዓዊ መብት ጥሰት ውስጥ ያልተካተቱት እነሱ ለዘብተኛ ሙስሊሞች ናቸው። እዚህ ላይ አሸባብን ወይም የነሱን አጋሮች ማለቴ አይደለም፤ ሌሎች አሉ በርካታ ወግ አጥባቂ ሙስሊሞች  ጥቃትን የሚቃወሙ፤ ለምሳሌ አሊ ፍላህ፤ ከግብፅ ሙስሊም ወንድማማቾች ጋ ጥብቅ ግንኙነት አላቸው፤ ሆኖም ሶማሊያ ውስጥ ለውጥ ካሳዩት ቡድኖች አንዱ ናቸው።  በተለይ በትምህርት እና ወላጅ አልባ ልጆች በመርዳቱ ረገድ ለውጥ ያመጡ! እኔ በበኬሌ አሊ ፍላህ ወይንም የሆነ ይህንን መንገድ የሚራመድ ሰው ኃይል ቢይዝ -  ለምዕብራባዊያን ርግጥም ሙስሊም ነው። ሆኖም ለሶማሊያ ጥሩ ዜና ነበር። ማጋነን አያስፈልግም። ሶማሊያ 100 ከመቶ የሙስሊም ሀገር ናት!

ያለፈው ሳምንት መጀመሪያ አዲስ የአንድነት መንግስት የመሰረተችው ምዕራብ አፍሪቃዊት ሀገር ማሊ፤ ከአዲሱ መንግስት ብዙ ትጠብቃለች። አዲሱ የማሊ የአንድነት መንግሥት ዋነኛው ተግባሩ በአክራሪ ሙስሊሞች እጅ የወደቀውን ሰሜን ማሊን መልሶ መያዝ መሆኑን አዲሱ የማሊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲማን ኮሊባሊ ማክሰኞ ዕለት ተናግረዋል። « ሰሜን ማሊን ከገባችበች ጭለማ ማውጣት ቅድሚያ የሚሰጠው ነው» ነው ያሉት ። በመጋቢት ወር በማሊ ከነበረው መፈንቅለ መንግስት በኋላ ከአልቃይዳ ጋ ግንኙነት አለው የሚባለው አክራሪ ሸማቂ እና የቱዓሬግ አማፂያን ፤ሰሜን ማሊን ተቆጣጥረው ሐገሪቱን ከፋፍለዋል።

Malians displaced by war gather at a makeshift camp in Sevare, about 600 kms (400 miles) northeast of the capital Bamako, July 11, 2012. The United States has called on Mali's authorities to accept offers by African states to send a military force to stabilise the country and help retake control of its vast northern desert, now in the hands of al Qaeda-linked Islamists. The U.N. Security Council has been reluctant to back military intervention without a clearer plan for the force. Meanwhile, regional criticism of Mali's army for a March coup has left soldiers there hesitant about the idea of foreign troops being dispatched. Picture taken July 11, 2012. REUTERS/Emmanuel Braun (MALI - Tags: POLITICS CONFLICT CIVIL UNREST)

ከሰሜናዊ ማሊ ቤታቸው የተፈናቀሉ ማሊያውያን

የመጀመሪያው የሽግግር መንግስት በአገሪቱ አብዛኛ ክፍል ተቀባይነት አልነበረውም። የቱዓሬግ አማፂያን እና ሙስሊም ተዋጊዎች በአገሪቱ ያለውን አለመረጋጋት ተጠቅመውበታል። ይህም ለመጀመሪያው የሽግግር መንግስት አመፁ ከአቅሙ በላይ ሆኖበት ቆይቷል።

በምእራብ አፍሪቃ የምጣኔ ሃብት ማህበረሰብ ፤ በምህፃሩ ECOWAS አሳሳቢነት የተመሰረተው የማሊ አዲስ መንግሥት 31 ሚኒስትሮች አሉት። ከነዚህ ውስጥ ግማሹ በመጀመሪያው የሽግግር መንግስት ያገለግሉ ናቸው። ከዚህ መንግስት አዲስ ነገር ቢኖር ከሁሉም የሀገሪቷ ትላላቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወከሉ ፖለቲከኞች የካቢኔ መቀመጫ (የሚንስትርነት ስልጣን) ማግኘታቸው ነው።  በቡርኪናፋሶ ዮንቨርሲቲ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ሉክ ኢብሪጋ  -መፈንቅለ መንግስት ካካሄዱት አራቱ አሁን የሚንስትርነት ቦታን በመያዛቸው የአገር ውስጥ መረጋጋት ሊፈጠር ይችላል የሚል እምነት አላቸው።

« ወሳኝ የሆኑት ሚኒስትሮች አሏቸው። ሰሜናዊውን ክፍል ማስመለስ መቻላቸውን እናያለን። ሌላው ደግሞ የኤክዋስን እርዳታ ይጠይቁ ይሆን ወይስ ማሊያውያን ብቻቸውን ችግራቸውን ይፈቱ እንደው ነው።»

Two young fighters of the Islamist group Movement for Oneness and Jihad in West Africa (MUJAO) walk in the streets of Gao on July 17, 2012. A group of armed youths has arrived in Gao from Burkina Faso, joining hundreds of other young African recruits who have come to sign up with radical Islamists controlling the northern Mali town. AFP PHOTO / ISSOUF SANOGO (Photo credit should read ISSOUF SANOGO/AFP/GettyImages)

አክራሪ የሙስሊም ሸማቂ

የቱአሬግ ህዝብን የወከሉት የቱሪዝም ሚኒስትሩ ኦስማኔ አግ ሪሳ ናቸው። እሳቸውም በሰሜናዊ ማሊ በርካታ ወሳኝ ሰዎችን እንደሚያውቁ እና ከአማፂዎቹ ጋ መደራደር እንደሚችሉ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል።

በአዲሱ  የብሔራዊ አንድነት መንግስት ውስጥ ግን ዋና ዋና የሙስሊሙ ቡድን ተጠሪዎች አልተካተቱም። ይህ ደካማ ጎናቸው ይሆናል ይላሉ ቻርለት ሄይል- በጀርመን GIGA ተቋም የምዕራብ አፍሪቃ ጉዳይ ተንታኝ፤ « በአካባቢው አንድነት እስኪመለስ እና መረጋጋት እስኪሰፍን ለማሊ ረዥም ጎዳና ነው። ፈጣን ስኬቶችን በርግጥ በቶሎ መጠበቅ አይቻልም። ከመጀመሪያው ከሽግግር መንግስት የተሻለ የመደራደር ብቃት ያለው ተስፋ የሚጣልበት መንግስት መመስረቱ  ራሱ የመጀመሪያው ርምጃ ነው።»

በሰሜናዊ የማሊ ክፍል አሁንም ሁኔታው አልተረጋጋም።  አክራሪው የሙስሊም ቡድን ከሮቡ ጀምሮ፤ የምዕራባዊያን ሙዚቃ በሬዲዮ እንዳይተላለፍ ከልክሏል።  የቡድኑ ቃል አቀባይ ኦሳማ ኦልድ አብደል ቃድር ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደገለፀው « ሰይጣናዊ» ሙዚቃ ማብቃት አለበት ፤ በዚህ ፋንታ የቁራን ጥቅሶች ይደመጣሉ ሲል አስታውቋል።

Religious leaders attend a memorial service for the 44 people killed in a wildcat strike at Lonmin's Marikana mine on August 23, 2012 in Marikana. Lonmin and nearby Impala Platinum closed for the day as workers prepared for memorials, including the main national service at Marikana where police gunned down 34 miners a week ago after deadly clashes had already claimed 10 people. The service at Lonmin will be the focal point during a day of mourning that will stretch across the country, as many of the victims were migrant workers whose bodies have already returned to their home villages. AFP PHOTO / STEPHANE DE SAKUTIN (Photo credit should read STEPHANE DE SAKUTIN/AFP/GettyImages)

ለ34ቱ የማዕድን ቆፋሪዎች የተደረገ የመታሰቢያ ሥነ ስርዓት

ደቡብ አፍሪቃ ዛሬም በድንጋጤ ላይ ትገኛለች። የደቡብ አፍሪቃ ፖሊስ ባለፈው ሳምንት አድማ በመቱ ሎንማይን በተሰኘው  የብሪታንያ  የማዕድን ኩባንያ ሠራተኞች ላይ

ተኩስ ከፍቶ 34  ሠራተኞች በጥይት መገደላቸው ይታወሳል። በዚህም ሳምንት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ለሞቱት የመታሰቢያ ሀዘን ሲካሄድ ቆይቷል።

በመታሰበያ ስነ ስርዓቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ፤ ባለስልጣናት፣ የሐይማኖት አባቶችም ይሁኑ የቤተሰቡ አባላት ችግሩ በሰላም እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል። ከሳምንቱ መጀመሪያ አንስቶ በማዕድን ማውጫው የተገኙት የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የጋራ ኮሚቴ ሊቀመንበር ኃላፊ ኮሊንስ ቻባኔ ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ ሲያቀርቡ፤« ይህ ለደቡብ አፍሪቃ አሳዛኝ ቀን ነው። በአንድ ላይ በመሆን ቀሪ ቤተሰቦችን እና በህክምና ላይ የሚገኙትን እንተባበራቸው እና ለሰላም እንስራ።»

ፖሊስ በማዕድን አውጪ ሰራተኞች ላይ በተከፈተው ተኩስ ከሞቱት ሌላ 78 የሚደርሱ ሰዎች ቆስለዋል።  ከሟቾቹ 28ቱ የኢምታታ ነዋሪዎች ነበሩ። በዚህ እና በጆሀንስበርግ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ በተገኙበት ማሪካና፤  ሰዎች በሀዘን ተሞልተው ነበር።

ከማዕድን አውጪ ቤተሰብ ፤ ኖንታማዞ ምቴምቡ የሎንማይን ኩባንያ ለቤተሰቡ አስተዳዳሪ ለነበሩት ቀሪ ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፍል ጠይቀዋል። «ፀሎቴ የተጠቂ ቤተሰብ አባላት በሙሉ ከማዕድን ኩባንያው እና ከባለስልጣናቱ ድጋፍ እንዲያገኙ ነው። እነዚህን ቤተሰቦች መመልከት የሚያሳዝን ነው።»

Women carry placards as they chant slogans to protest against the killing of miners by the South African police on Thursday, outside a South African mine in Rustenburg, 100 km (62 miles) northwest of Johannesburg, August 17, 2012.South African Police were forced to open fire to protect themselves from charging armed protesters at the Marikana mine, and 34 of the protesters were killed, Police Commissioner Riah Phiyega said on Friday.She told a news conference that 78 people were injured and 259 arrested in Thursday's violence. The police members had to employ force to protect themselves from the charging group, Phiyega said. REUTERS/Siphiwe Sibeko (SOUTH AFRICA - Tags: CIVIL UNREST CRIME LAW)

አድማ የመቱ የሎንማይን ኩባንያ ሰራተኞች

የካሳ ጥያቄ ብቻ አይደለም የደቡብ አፍሪቃን ህዝብ እያነጋገረ ያለው። የማዕድን ቆፋሪዎቹ ለምን ተገደሉ? ዋናው ርዕስ ነው።  የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚዳንት ጄኮብ ዙማ ጉዳዩን የሚከታተል የገለልተኛ ኮሚቴ ስም ዝርዝር ይፋ አድርገዋል። «ኮሚቴው መስሪያ ቤቱ በቀጥታም ይሁን ቀጥታ ባልሆነ መንገድ የሰው ህይወት የጠፋበትን ወይንም ንብረት የወደመበትን ምክንያት ስለመሆኑ ይመረምራል።»

ሲሉ ነው ዙማ ያለፈው ሀሙስ ያስታወቁት። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሎንማይን ማዕድን ቆፋሪዎች ፤ አስተዳደሩ የደሞዝ ጭማሬ ጥያቄያቸውን ከተቀበለ፣ የተሻሻለ የስራ ሁኔታ ከፈጠረ እና  ለማቾቹ የቀብር ስነስርዓት ሙሉ ድጋፍ ካደረገ፤ ሰኞ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ አሳውቀዋል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

መስፍን መኮንን

Audios and videos on the topic