ትኩረት በአፍሪቃ፦ የቱኒዝያ ምርጫ፤ የሱዳን አቤቱታ | አፍሪቃ | DW | 12.10.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ትኩረት በአፍሪቃ፦ የቱኒዝያ ምርጫ፤ የሱዳን አቤቱታ

የሰሜን አፍሪቃዊቷ አገር ቱኒዚያ ባለፈው ሳምንት የእንደራሴዎች ምርጫ አካሂዳለች። ቀደም ሲል የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያካሄደች ሲሆን፣ በነገው እሁድ ዕለትም የማጣሪያውና የመጨርሻው ምርጫ ይደረጋል። ባለፈው ነሐሴ ወር የተመረጠው አዲሱ የሱዳን የሽግግር መንግስት ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ ሱዳንን ከአሸባሪ አገሮች ዝርዝር ውስጥ እንድታወጣት ጠይቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:14

ትኩረት በአፍሪቃ፦ የቱኒዝያ ምርጫ፤ የሱዳን አቤቱታ

የሰሜን አፍሪቃዊቷ አገር ቱኒዚያ ባለፈው ሳምንት የእንደራሴዎች ምርጫ አካሂዳለች። ቀደም ሲል የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያካሄደች ሲሆን፣ በነገው እሁድ ዕለትም የማጣሪያውና የመጨረሻው ምርጫ ይደረጋል። የምክር ቤት ምርጫው የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ግን፣ ባለፈው ረቡዕ የተገለጸ ሲሆን፣ አንድም ፓርቲ መንግስት ለመመስረት የሚያስችለውን መቀመጫ ቁጥር አላገኘም። በቱኒዚያ ከሁለት መቶ በላይ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ። በምርጫ የተሳተፉት ግን 10 ብቻ ናቸው። ይህ የጸደይ አብዮት የተጀመረባት የምትባለዋን አገር የምርጫ ሂደት እና ተግዳሮቶቹን የሚዳስስ ይሆናል የመጀመሪያው የ"ትኩረት በአፍሪቃ" ክፍል። 

ባለፈው ነሐሴ ወር የተመረጠው አዲሱ የሱዳን የሽግግር መንግስት ዩናይትድ ስቴትስ ሱዳንን ከአሸባሪ አገሮች ዝርዝር ውስጥ እንድታወጣት ጠይቋል። በአሸባሪነት ይከሰስ የነበረው መንግስት በህዝባዊ ተቃዉሞ ስልጣን ለቅቋልና ሱዳን በዝርዝሩ ውስጥ ልትቆይ አይገባትም ነው የሱዳን መንግስት ክርክር። ሁለተኛው የ"ትኩረት በአፍሪቃ"   የዝግጅት ክፍል በዚህ የሱዳን ጥያቄ ላይ የሚያተኩር ነው። 

ሙሉ ዝግጅቱን የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ። 

ገበያው ንጉሴ

ልደት አበበ

 

Audios and videos on the topic