ትኩረት ለዝዋይ ሐይቅ | ጤና እና አካባቢ | DW | 25.12.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ትኩረት ለዝዋይ ሐይቅ

የሐሮማያ ባህር በ1970ዎቹ ወደ ስምንት ሜትር ከፍታ ነበረው። ይህ ሐይቅ ለብዙ የአከባቢው አርሶ አደሮችና አሣ እስጋሪዎች የኑሮዋቸው ዋስትና ነበር። ንጹህ የመጠጥ ውሃም ለአከባቢው ከዚው ባህር ይገኝ እንደነበር ይነገራል። ከዚህም አልፎ ለአከባቢው ህዝብና ከሌላ ሥፍራ ለሚመጡም ጎብኚዎች የመዝናኛ ስፍራ ነበረ።

default

ባከባቢው በባህሩ ምክንያት ይካሄድ የነበረ የመስኖ እርሻ ሥራና በስፍራው የሚገኝ ደን መጥፋት ከአየር ለውጥ ጋር አንድ ላይ በመሆን ነበር ይህን ብዙ የተባለለትን ባህር ሞት ያፈጠነው። ባከባቢው የሚገኝ ህዝብ ወደ ውሃው ከሚገባው የውሃ መጠን በላይ ይጠቀም እንደ ነበር የስነ- ምድር ባለሙያዎች ይናገራሉ። የሐሮማያ ሐይቅ ገጣሚው እንዳለው እንደ ሰው ሞቷል። ተመልሶ የመምጣቱ ጉዳይ ያው ለፈጣሪ እንተወውና አሁን እንደ ሐሮማያ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያ ውስጥ  ያሉ ኃይቆችስ የአረመያ እጣ ፈንታ ይገጥማቸው ይሆን?ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪቃ የውሃ ማማ ናት ትባላለች።  አባይ፣ ዋቢ ሸበሌና አዋሽ የመሳሰሉና  ረዣዥም ወንዞች በብዛት  በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሀይቆችም አሏት። ከስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ውስጥ ዝዋይ አንዱ ነው። የዝዋይ ሐይቅ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በ60 ሜትር ርቀት ላይ በኦሮሚያና ደቡብ ህዝቦች ክልሎች አዋሳኝ ድንበር ላይ ይገኛል። 31 ኪሎሜትር ርዝመት ሲኖረው ስፋቱ 20 ኪሎሜትር፣ ጥልቀቱም ዘጠኝ ሜትር ነው።  የዝዋይ ሐይቅ የተለያዩ ለዓይን ማራኪ የሆኑ የተፈጥሮ ሐብቶች አሉት።  በአዕዋፍና በአውራሪስ ብዝሀ ህይወትም የታወቀ ሐይቅ ነው። በብዙ ቶን የሚገመት የአሣ ምርት በየዓመቱ ከባህሩ ይገኛል። ፕሮፌሰር ብሩክ ለማ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የውሃ አዘል መሬቶች ሥነ-ምህዳር መምህርና ተመራማሪ ናቸው። የሐሮማያ ኃይቅን በቅርበት እየተከታተሉ የነበሩ ተመራማሪ ሲሆኑ ከኃይቁ መጥፋት መንስሔዎች ጋር በተያያዘም ጥናት አካሂደዋል።

ገመቹ በቀለ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic