ትራምፕ ምርጫ ይራዘምን በማድበስበስ አስተባበሉ | ዓለም | DW | 31.07.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ትራምፕ ምርጫ ይራዘምን በማድበስበስ አስተባበሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሕዳር 2020 የሚጠበቀዉ ምርጫ ይራዘም ብለዉ መጠየቃቸዉን አላልኩም አይነት መልስ በመስጠት አድበሰበሱ። ትራምፕ የኮሮና ወረርሽኝ ስጋትን ተከትሎ በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫው ቢራዘም ዜጎች ደህንነታቸው ጠብቀዉ ፣ ምርጫዉን ማካሄድ ይችላሉ ሲሉ ተናግረዉ ነበር።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሕዳር 2020 የሚጠበቀዉ ምርጫ ይራዘም ብለዉ መጠየቃቸዉን አላልኩም አይነት መልስ በመስጠት አድበሰበሱ። ትራምፕ የኮሮና ወረርሽኝ ስጋትን ተከትሎ በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫው ቢራዘም ዜጎች ደህንነታቸው ጠብቀዉ ፣ ምርጫዉን ማካሄድ ይችላሉ ሲሉ ተናግረዉ ነበር። ፕሬዚዳንቱ ቀደም ብለዉ ምርጫ ይራዘም ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄያቸዉን ፤ የምርጫ ቀጠሮ ቀን እንዲቀየር አልፈለኩም ሲሉ በማድበስበስ  አስተባብለዋል። እንድያም ሆኖ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ምርጫው በፖስታ ቤት አገልግሎት የሚካሄድ ከሆነ ከፍተኛ መጭበርበር ይከሰታል ሲሉ አሁንም ግምታቸዉን ተናግረዋል። ቀደም ሲል ፕሬዚዳንቱ  ባቀረቡት ጥያቄ በአሜሪካ ፌዴራል መንግስት ምክር ቤት በራሳቸዉ የሬፑብሊካን ፓርቲ እና በተቃዋሚዉ ዴሞክራቶች ፓርቲ አባላት ከፍተኛ ተቃዉሞ ገጥሞአቸዋል። በዩናይትድ ስቴትስ አንድ ፕሬዚዳንት ምርጫን የማራዘም ሙሉ መብት የለዉም። በዩናይትድ ስቴትስ ምርጫን ማራዘም የሚቻለዉ የአሜሪካ ኮንግረስ ማለት ሴኔቱ እና የተወካዮች ምክር ቤት ስምምነት ላይ ሲደርሱ ብቻ ነዉ።  

 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ

ተዛማጅ ዘገባዎች