ትራምፕ ሃምዛ ቢን ላደን መገደሉን አረጋገጡ | ዓለም | DW | 14.09.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ትራምፕ ሃምዛ ቢን ላደን መገደሉን አረጋገጡ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ፕራምፕ  የአልቃይዳ የቀድሞ መሪ ኦሳማ ቢን ላደን ልጅ ሃምዛ ቢን ላደን መገደሉን አረጋገጡ። መቼ እንደተገደለ ግን አልገለፁም።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ፕራምፕ  የአልቃይዳ የቀድሞ መሪ ኦሳማ ቢን ላደን ልጅ ሃምዛ ቢን ላደን መገደሉን አረጋገጡ። ሀምዛ የተገደለው በአሜሪካ የፀረ-ሽብር ተልኮ አፍጋኒስታን እና ፓኪስታን አካባቢ ነው ይላል ዛሬ ከኋይት ሀውስ ይፋ የሆነው መግለጫ ። መግለጫው ግን ልጅየው መቼ እንደተገደለ አይገልፅም። ይሁንና የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን የስለላ ድርጅትን ዋቢ በማድረግ ባለፈው ሐምሌ ወር መጨረሻ ሀምዛ ቢን ላደን ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ መገደሉን ዘግበው ነበር። ከኋይትሀውስ የወጣው የዛሬው መግለጫ የቢን ላድን ልጅ መገደል ለአልቃይዳ ቡድን ሽንፈትን ብቻ ሳይሆን  ቡድኑ ያሉትን ወሳኝ እንቅስቃሴዎች ይቀንሳል ይላል። ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው የካቲት ወር የቢን ላደን ልጅ ያለበትን ቦታ ለሚጠቁም አንድ ሚሊዮን ዶላር እንደሚሰጥ ይፋ አድርጋ ነበር። ሀምዛ ቢን ላደን አባቱ ከተገደለ በኋላ የአሸባሪው አልቃይዳ ቡድን አንዱ ተተኪ መሪ ነበር ተብሎ ይታመናል።

ልደት አበበ

እሸቴ በቀለ