ታፍነዉ የተወሰዱት የጋምቤላ ሕጻናት | ኢትዮጵያ | DW | 05.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ታፍነዉ የተወሰዱት የጋምቤላ ሕጻናት

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ባለፈዉ ወር ከጋንቤላ ታፍነዉ ከተወሰዱት ሕጻናት መካከል 100 ሕጻናት ያሉበት ቦታ መታወቁን የሱዳን ትሪቡነ የተሰኘዉ ድረ ገፅ አስነብቦአል። እንደ ዘገባዉ ከሆነ ታፍነዉ የተወሰዱትን ሕጻናት ፍለጋ ላይ ርዳታዉን ለመስጠት የኢትዮጵያ ጦር የደቡብ ሱዳንን ድንበር አቋርጦ አካባቢዉ ላይ ይገኛል።


ከደቡብ ሱዳን በመጡ የሙርሌ የጎሳ አባላት ታፍነዉ የተወሰዱት ሕጻናት አሉበት የተባለዉ ቦታ ከሰሜናዊ ከደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ 300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መሆኑኑን የደቡብ ሱዳን መንግሥት ቃል አቀባይ አቴኔ ዌክ አቴኔ መግለፃቸዉ ሱዳን ትሪቡነ ዘግቦአል። እንደ ዘገባዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ጦር ሠራዊት እቦታዉ ላይ በመገኘት ሁኔታዉን እየተቆጣጠረ መሆኑን የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ ረዳ ማረጋገጣቸዉም ተዘግቦአል። በፌዴራል እና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አበበ ወርቁ እንዳሉት ከጋንቤላ ታፍነዉ የተወሰዱት ሕጻናት ያሉበት ቦታ ታዉቋል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic