ታዋቂው የጀርመን ደራሲ ኅልፈት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 14.04.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ታዋቂው የጀርመን ደራሲ ኅልፈት

ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው በ87 ዓመቱ ሰኞ ሚያዝያ አምስት ቀን፣2007ዓ.ም ነው። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በጀርመን ስነ ጽሑፍ ላይ ጉልህ አሻራውን አሳርፏል። የዓለም ሎሬት ማዕረግ ሽልማትንም ተጎናጽፏል፤ ደራሲ ጉይንተር ግራስ። ይኽ ደራሲ በጀርመን የስነጽሑፍ ታሪክ እጅግ ከፍተኛ ድርሻ አለው፤ አወዛጋቢነቱም የዛኑ ያህል ነው።

የዛሬ ሦስት ዓመት « መነገር ያለበት» ሲል SüddeutscheZeitung በተሰኘው ጋዜጣ ላይ በጀርመንኛ ያቀረበው ግጥም እጅግ ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ነበር። «በብዕር ቀለሜ ጠብታ ፍፃሜ፥ በስተርጅናው ዘመኔ፥ መነገር ያለበትን ለወገኔ» በማለት የእስራኤል እና የኢራን የኑክሌር ይዞታን በማነፃጸር ትችታዊ ስንኝ ቋጥሮ ነበር። በዚህ ጽሑፉ በወቅቱ «ጸረ-ሴማዊ» በሚል ከፍተኛ ነቀፌታ ደርሶበታል። ከዚህ ዓለም ከተለየ ዛሬ አንድ ቀን አስቆጥሯል። ስለ ደራሲ ጉይንተር ግራስ ሕይወት እና ኅልፈት ሜኽትሂልድ ሜስከር ያዘጋጀውን ይልማ ኃይለሚካኤል እንዲህ ያቀርበዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማጫወቻ ይጫኑ።


ሜኽትሂልድ ሜስከር /ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች