ታዋቂዋ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ወጣት ሙዚቀኛ | ባህል | DW | 28.01.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ታዋቂዋ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ወጣት ሙዚቀኛ

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ 114 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዉ ወሊሶ ከተማ ነዋሪ የሆነችዉ ወጣት ኪያ ተስፋዬ በከተማዋ በሚገኝ ፍርድ ቤት በፀሐፊነት በኮምፒዉተር ባለሞያነት ታገለግላለች። በፌስ ቡክ መገናኛ መረብ ምታቀርባቸዉ ሙዚቃዎችዋ ከ 40 ሺህ በላይ ተከታዮችንም አፍርታለች።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:34

ኪያ ተስፋዬ

የታዋቂዋ ኢትዮጵያዊት ከያኒ የአስቴር አወቀ ሙዚቃ ከምንም በላይ የምወዳቸዉ ናቸዉ። አስቴርን ፈለግ እከተላለሁ ያለችን በፌስ ቡክ የመገናኛ መረብ  ላይ በምታቀርባቸዉ ሙዚቃዎችዋ፤ በሐገርም ሆነ በዉጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ ታዋቂነትን አትርፋለች፤ ወጣት ኪያ ተስፋዬ  ፅዮን ትባላለች። ወጣት ኪያ በፌስ ቡክ ማኅበራዊ መገናኛ መረብ 45, 890 ተከታዮች አላት። አሁን አሁን ግን አካባቢዉ ላይ የፊስ ቡክ መገናኛ መረብ በመዘጋቱ ወደ ወደ ፌስቡክ የማቀርባቸዉ ሙዚቃዎቼም ሆኑ ከማገኛቸዉ የመረቡ ጓደኞቼ ጋር ከተገናኘን ቆየን ስትል አጫዉታናለች።  ወጣት ኪያን የእለቱ እንግዳችን አድርገናታል።  

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ 114 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዉ ወለሲ ከተማ ነዋሪ የሆነችዉ ወጣት ኪያ ተስፋዬ በከተማዋ በሚገኝ ፍርድ ቤት በፀሐፊነት በኮምፒዉተር ባለሞያነት እንደምታገለግል ገልፃልናለች። እሁድና ቅዳሜ ማታ ማታ በኦሮምያ በወሊሶ ኦሮምያ ስቴትስ ዩንቨርስቲ በሒሳብ ትምህርት ማለት አካዉንቲንግ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ ስትሆን በዚህ ዓመት እንደምትመረቅም ነግራናለች።    

አባቴ የኔ ሲል በኦሮምኛ እንደሰየሟት የምትናገረዉ ኪያ ተስፋዬ የአቧትዋን ፈለግ በመከተል ወደ ኪነ-ጥበቡ ዓለም በጥልቅ ለመግባት ጥረት የጀመረችዉ ቀደም ሲል ጀምሮ ነዉ የዛሬ አራት ዓመት ገደማ አዲስ አበባ ላይ አይድል የሙዚቃ ዉድድር ላይ ተሳትፋ በአራተኛዉ ዙር ላይ በለስ ሳይቀናት ከዉድድሩ ብትገለልም ቤተሰቦችዋ ከመጀመርያዉ ጀምሮ ርዳታ እያደረጉላት እንደሆን ወጣት ኪያ ተናግራለች።

ወጣት ኪያ ተስፋዬ የጂጂ ሺባባዉ አድናቂ በመሆንዋ በርካታ ዜማዎችዋን አስመስላ በማዜምዋ በፌስ ቡኩ የመገናኛ መድረክ በተለይ በርካታ አድናቂዎችን አፍርታለች። አሁን አሁን ዝናን እያተረፈ የመጣዉ የሃጫሉ ሁንዴሳ አድናቂም በመሆንዋ የሃጫሉን ዘፈኖች አስመስላ ማዜምን ጀምራለች።

በሊቢያ ኢትዮጵያዉያን በአይሲስ ፅንፈና ቡድን በተገደሉበት ወቅት ኪያ ተስፋዬ በሥነ ግጥም ኃዘንዋን ገልፃ በዚሁ በመገናኛ መረብ ፌስቡክ ለተከታዮችዋ አካፍላለች። አካፍላም ነበር።  ከኪያ ጋር ያደረግነዉን ሙሉዉን ቃለምልልስ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic