ታሪካዊዉ የኃይል ምንጭ፤ ከሰል | ጤና እና አካባቢ | DW | 19.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ታሪካዊዉ የኃይል ምንጭ፤ ከሰል

ከሰል በአብዛኛዉ የአፍሪቃ ሀገራት ለቤት ዉስጥ አገልግሎት የሚፈለግ የኃይል ምንጭ ነዉ።

default

ከሰል ለማግኘት ደግሞ እንጨት ይፈለጋል፤ እንጨት ለማግኘት ዛፍ ይቆረጣል። ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ዉስጥ ይህን አስመልክቶ የተሰራ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተዉ ወደ66 ሺ ገደማ ቶን ከሰል ለማምረት ወደአንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ዛፎች ይጨረጨፋሉ። ጥራቱን የጠበቀ ከሰል የሚገኘዉ ከአገር በቀል እና እድሜ ጠገብ ዛፎች በመሆኑ የብዝሃ ህይወት ስብጥር መጉዳቱ፤ አካባቢን ማራቆቱ ሳያንስ፤ ከሰል የሚከስልባቸዉ አካባቢዎች መሬት ለእርሻም ሆነ ለግጦሽ እሚበጅ አይሆንም ዉስጡ በሚጠራቀመዉ ካርቦን ሞኖክሳይድ ሰበብ! ወደከባቢ አየር የሚለቀቀዉ አደገኛ ጋዝም ተፅዕኖ ቀላል አይደለም። ግን ደግሞ ከሰል የብዙሃኑ ህዝብ የጓዳ ምሰሶ፤ የምድጃ አጋር ነዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ