ታላቅ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ | ባህል | DW | 22.10.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ታላቅ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ

የማንበብ ልምድ በተለይ በአዉሮጻ እና በአሜሪካ ስር የሰደደ መሆኑ በእነዚህ ክፍለ አለም በሚኖሩ ህዝቦች ዘንድ የማንበብ ባህል አለ ለማለት በርግጥ ያስደፍራል

የጀርመንን የሰላም ስነ-ጽሁፍ ተሸላሚ ሳዉል ፍሪድ ሌንደር,ከፕሪዝደንት ሆርስት ኮለርና ባለቤታቸዉ

የጀርመንን የሰላም ስነ-ጽሁፍ ተሸላሚ ሳዉል ፍሪድ ሌንደር,ከፕሪዝደንት ሆርስት ኮለርና ባለቤታቸዉ

በፍራንክፈርት ከተማ ለአምስት ቀናት በአለም በትልቅነቱ የተነገረለትን የመጸሃፍ አዉደ-ርእይን በማስመልከት በባህል መድረካችን ዘገባ ልንሰራ ስንነሳ በተለይ በአዉሮፓ እና በአሜሪካ ስለሚታየዉ የማንበብ ባህል አወሳንንና ፣ በአዉሮጻ ከሚገኙ አገሮች ዉስጥ በማንበብ የሚታወቀዉ ህዝብ የትኛዉ ነዉ ስንል ጥያቄያችንን አነሳን አንዳንዶች ሩስያ አንዳንዶች ደግሞ እንግሊዞች ሌሎች ደግሞ አይ የእስካንዲኒንቪያን አገር ህዝቦች ናቸዉ ይላሉ። የባህል መድረካችን በዚህ ርእስ መልስ ይሰጠን ይሆን? ስለ ፍራንክፈርቱ የመጸሃፍ አዉደ-ርዕይ ስለ ኖቤል ተሸላሚዎቹ ጻህፍት የዛሪ የባህል መድረካችን በጥንቅሩ አካቷል መልካም ቆይታ